You are currently viewing ግልፅ  ስለማድረግ  የአማራ ሕዝባዊ ኃይል APF (ፋኖ) መስራችና  አመራር  እንደመሆኔ  መጠን  ለሚመጡ ጥያቄዎች ግልፅ ማብራርያ መስጠት ይጠበቅብኛል ብዬ አስባለው፦  ሰሞኑን በርካታ ቁጥር…

ግልፅ ስለማድረግ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል APF (ፋኖ) መስራችና አመራር እንደመሆኔ መጠን ለሚመጡ ጥያቄዎች ግልፅ ማብራርያ መስጠት ይጠበቅብኛል ብዬ አስባለው፦ ሰሞኑን በርካታ ቁጥር…

ግልፅ ስለማድረግ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል APF (ፋኖ) መስራችና አመራር እንደመሆኔ መጠን ለሚመጡ ጥያቄዎች ግልፅ ማብራርያ መስጠት ይጠበቅብኛል ብዬ አስባለው፦ ሰሞኑን በርካታ ቁጥር ያለው አባላትና ደጋፊዎቻችን ከ ሐገር ውስጥ እስከ ውጭ ድረስ አፋኝ ግብረ ሐይሉ ማሳደዱን እዳቆመ ፡ይህን እንዳረጋግጥላቸው ጠይቀውኛል። በግሌ ያለኝ ምልከታ …እና እውነታው መንግስት የሕግ ማስከበር የሚል ስያሜ የሰጠው የማፈን ተግባር በእኔ ምልከታ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ትናንት በአዴት ወንድማችን በላይነህ መታፈኑ ከሰባታሚት ማረሚያ ሕግ የፈታቸውን የፋኖ አመራሮች የፌዴራል መንግስት አፍኖ ለመውሰድ የሚያደርገው ግብ ግብ ግልፅ ማሳያ ነው። እኔ የማውቀው ዛሬም አባሎቻችን በእዬ ሜዳው እዬተሳደዱ የክረምት ዝናብ ላያቸው ላይ እዬወረደባቸው ነው። ዛሬም ወንድሞቻችን በእዬ ማጎሪያ ቤቱ ታጉረው እዬተሰቃዩ ይገኛሉ ፣ ዛሬም በፋኖነታቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል እዬተፈናቀሉም ነው። ዛሬ ጓዶቻችን በመራዊ ፡ ዳንግላ ፡ቡሬ ፡ፍኖተ ሰላም ፡ደንበጫ ፡አማኑኤል፡ ኮርክ ባሶ ሊበን ፡ ማርቆስ ፡ደጀን ፡ሸበል ፡ቢቸና ፡ሞጣ ፡ወይን ውሃ ፡ አዴት፡ ሸዋ ወሎ ጎንደር እና ፡መሰል ቦታዎች በግልፅ የሚሳደዱ ጓዶች አሉን ። እውነታው ይህ ሁኖ ሳለ መንግስት ሕግ ማስከበሩን ትቸዋለው ብሎኛል ማለት በሚሳደዱ ወንድሞቻችን መሳለቅ ይመስለኛል። አንዳንድ ወረዳዎች ላይ እራሱ የብልፅግና አመራሮች ፋኖነት ወንጀል አይደለም ወንድሞቻችንን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ በጎ አመራሮች እንዳሉ እናውቃለን ።ይህ የተቀደሰ ሃሳብ ነው ምስጋናም ይገባቸዋል። ሌላኛው ጉዳይ አንድ አንድ አመራሮቻችንም ሆነ አባሎቻችን በግላቸው በሚያደርጉት ግኑኙነት ነፃነታቸው ታውጆላቸው ከሆነ አይከፋኝም ደስተኛም ነኝ እነደ ሕዝባዊ ኃይሉ ግን የምናቀው አቅጣጫ የለም። መንግስት የሕግ ማስከበሩን ዘመቻ አቁሞ ከሆነ የማንደራደርባቸው ቀይ መልመሮች ሊቀመጡስ አይገባም ወይ? – የሚሳደዱ ጓዶቻችን እና አመራሮቻችን ዋስትና -በእዬ ማጎርያው የሚገኙ አባሎቻችት ጉዳይ -ያለ ምንም ጥፋት ከስራ ገበታቸው የተባረሩ አመራርና አባሎቻችን ጉዳይ – ቀጣይ የፋኖ እንቅስቃሴ እና የአማራ የትግል አቅጣጫዎች ወ ዘ ተ የሚሉት ጉዳዮች እንዴት ታይተው ይሆን? በአጠቃላይ እኔም ሆንኩ የተወሰኑ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል አመራሮች የሕግ ማስከበር የሚል ስያሜ የተሰጠው ዘመቻ መቋረጡ እውቅናው ስለሌለን አባሎቻችን ተዘናግተው አላስፈላጊ መስዋትነት እንዳትከፍሉ መዘናጋት እንደሌለባችሁ ለማሳሰብ እወዳለው። ክፋት ለማንም ” በጎነት ለሁሉም” ላንጨርስ አልጀመርንም !! ትግላችን እስከ ነፃነት ማማች ነው ! © አየለ አስማረ ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply