You are currently viewing ግሎባል አሊያንስ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች 7 ነጥብ5 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም…

ግሎባል አሊያንስ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች 7 ነጥብ5 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም…

ግሎባል አሊያንስ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች 7 ነጥብ5 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ግሎባል አሊያንስ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች 7 ሚሊየን 5 መቶ ሺህ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉ የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳደሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደና የግሎባል አሊያንስ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችና የግሎባል አሊያንስ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል፡፡ የግሎባል አሊያንስ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ ለተፈናቃይ ወገኖች ባደረጉት ንግግር በአሜሪካን ሀገር በሂውስተን፣ በፍሎሪዳ፣ በፍላደልፊያና ናሽቪል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የግሎባል አሊያንስ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ለተቸገሩ ወገኖቻችን ድረሱላቸው ብለው በሰጡን ገንዘብ ድጋፉን አምጥተናል ብሏል፡፡ በዚህም 2ሺህ 250 ብርድልብስ፣ 1ሺህ 200 ኩንታል ዱቄትና 2 ሺህ200 ፍራሽ አምጥተናል ብሏል፡፡ ድጋፉ ችግሩን ይፈታል ብለን ሳይሆን ወገን እንዳላችሁ እንድታውቁ የተደረገ ድጋፍ ነው ሲል ገልጿል፡፡ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግሯል። የግሎባል አሊያንስ የሀገር ውስጥ አስተባባሪ አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ ክፉዎች እንዳሉ ሁሉ ደጎችም ስላሉ በመላው ዓለም የሚገኙ ደግ ኢትዮጵያዊያን ባዋጡት ገንዘብ ድጋፍ አምጥተናል ብለዋል፡፡ ተፈናቅላችሁ በመጠለያ ጣቢያ ያላችሁ ሕፃናት፣ አዛውንቶች፣ሴቶችና ሌሎች በመላው ዓለም ወገን አላችሁ እንዳይከፋችሁ ብሏል፡፡ የተፈለገው አንገት ማስደፋት ነው ነገር ግን አንገት አንደፋምም ነው ያለው፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው ተፈናቃይ ወገኖች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። አሚኮ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply