ግሎባል አሊያንስ ኢትዮጵያ ለተፈናቃይ ወገኖች ከ8.5 ሚሊየን በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡በአርቲስት እና በሰብአዊ መብት ተማጋች ታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አሊያስ በደብረ ብ…

https://cdn4.telesco.pe/file/YyTInoX86rRE4n7AXNO8yTZXXXk_QhD-wOyIyqn4B6MiIIGRNADVJQffirKqhctVt50DjC5WQsIGruXtpwEmZAHhVaFhpE6g_mp1aef9LBBpWjXJirrpuXHVUrP8OkQrjxpw1h9h3t4JrMkW6G6vpRuHlHPs_dZAahNyiOVG0tsoor8Q1yJ1BvON-XnshjQghv2S-ZNZj8P4VMWBxjXQ3cD7xLA5aomwBBKVwu5Py_BgQgZOHsVmHkoxCz8yOe9qDiQqa09KLpEu63024px1LJtzw2MBc6uI3a1Q2Uad0lLTA37K7_ksGi0F9lKF8kVOZ4kfvP1fHd9gVlsKWh36Lw.jpg

ግሎባል አሊያንስ ኢትዮጵያ ለተፈናቃይ ወገኖች ከ8.5 ሚሊየን በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

በአርቲስት እና በሰብአዊ መብት ተማጋች ታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አሊያስ በደብረ ብርሀን ለሚገኙ ተፈናቃይ ዜጎች የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የግሎባል አሊያንስ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ እና መስራች አርቲስት ታማኝ በየነ በደብረብርሀን በመገኘትም ድጋፉን እርክክብ አድርጓል፡፡

ህውሀት የተባለው የሰይጣን ፈረስ ባስከተለው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜገች በተቻለው አቅም ሁሉ ለመርዳት ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑን አርቲስት ታማኝ ተናግሯ፡፡

ያለ ፍላጎታቸው ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ደጅ ላይ ወድቀዋል ዜጎቻችን ለመረዳት እራሳችን እንበቃለን የሚል መልእክትም አስተላፋል፡፡

ግሎባል አሊያንስ ከህጻናት መብት እና ወንጀል መከላከል ጋር ከሚሰራው የኡጋንዳ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ድጋፉን ያደረገው፡፡

በድጋፉም በክልሉ ጥያቄ መሰረት 3ሺህ ብርድ ልብስ 3ሺህ ፍራሾች እና 800 ኩንታል ዱቄት ነው ድጋፍ ያደረጉት፡፡

ግሎባል አሊያንስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቆ በሚቀጥሉት ጊዜያትም በአፋር ክልል እና በጎንደር ሰብአዊ ድጋፉን እንደሚያደረግ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ከዚህ በፊት ለጤና ሚኒስትር ከ15ሚሊየን በለይ የሚገመት የጤና መመርመርያ ማሽኖችን ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply