ግማሽ የሚሆነዉ የአለም ህዝብ በ2035 ከመጠን በላይ እንደሚወፍር አንድ ጥናት አመለከተ፡፡የአለም አቀፉ ከመጠና በላይ ዉፍረት ፌዴሬሽን እንዳስታወቀዉ 51 በመቶ የሚሆነዉ የአለም ህዝብ በ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/J2DJMkZLKYsZSK9HedM2tgAql1r0iITgjObLyPupNAv1vcF5sDqOnKjGHDp8rQ22P0TKfSjR9miRggIoP-hsPyvHuVCEV3BYnn9BSVpDPziWpQqnaIVdLK5zvHm2v3oG400bpqePwLtUMg2HCNbs5xT56hUdEHU-9avVGoMioCuinc6Q5fyzF3JTXnE4Lc8l8OZhyu-8NejmmoO2pnpiEQ0aDs2vsD-dMoUwvFVrzqFMwKai9YHS5jp8meidcbMsMtmsXkxAoPnr_SN3aocAcmZFY6RDNZ3RhuL9x262L8iBNU-FrcDIjiEJFVoScHc8ZWH9MoUNedxLxeR61pdKbQ.jpg

ግማሽ የሚሆነዉ የአለም ህዝብ በ2035 ከመጠን በላይ እንደሚወፍር አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

የአለም አቀፉ ከመጠና በላይ ዉፍረት ፌዴሬሽን እንዳስታወቀዉ 51 በመቶ የሚሆነዉ የአለም ህዝብ በ2035 ከመጠን በላይ ይወፍራል፡፡

የአለም ህዝብ አመጋገቡን ካላስተካለና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካላደረገ በተጠቀሰዉ አመት ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ ለችግሩ ተጋላጭ ነዉ ተብሏል፡፡

አሁን ላይ 2.6 ቢሊዮን ዜጎች ለዚህ ችግር እንደተጋለጡ ፌዴሬሽኑ በሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ፌዴሬሽኑ ችግሩን ለመቀነስ ለጤና ጠንቅ የሆኑ በተለይም የስኳርና የጨዉ መጠናቸዉ ከፍ ያሉትን ምግቦች ማስወገድ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

ከ18 አመት በታች የሆኑ ከመጠን በላይ የሚወፍሩ ወንዶች ቁጥር በ2035 አሁን ካለዉ እጥፍ እንደሚጨምር ተነግሯል፡፡

በአንጻሩ የሴቶች ደግሞ በ125 በመቶ እንደሚያድግ አርቲ ኒዉስ የፌዴሬሽኑን ሪፖርት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በአባቱ መረቀ

የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply