ግራር የጠቢባን መናሀሪያ ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር ሠዓሊትን ፍለጋ የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡ግራር የጠቢባን መናሀሪያ ከዩኔስኮ አሽበርግ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ሴት ሠዓሊያንን ማብቃ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Yf2LpxyeNgFwRhqyJO4TFhgAc6MaaInY_sFoTPl8LM4Jt04NOZ0zUwRiY3SdjNVACFfRAkr4t24uQN03hDj1ZSOEDJiRkMWzNiUrncOfl42FSwHa6lRDBofozG7cgzlRV_AaP4hAW_9GN0mr2P5F0GkXFwybpR3PnjDIctW5renIdVrSpVOB0w95Txy9e9YAszRjzmG8lK_XTYbdMR0XGacHPf8TOMBrVpFznewGd4foINEsHnkWbhm9z3hVx-jkEETKH7HVUcoQ7n2zPPToiKvwe2Q7gn2zyEmPw61bsnA5alLi_eEuf0hAf-dXouh3R4YZJ9Oswtcy3UHWEByxzg.jpg

ግራር የጠቢባን መናሀሪያ ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር ሠዓሊትን ፍለጋ የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡

ግራር የጠቢባን መናሀሪያ ከዩኔስኮ አሽበርግ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ሴት ሠዓሊያንን ማብቃት ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል፡፡

የባህል ምርቶች እና የአርቲስቶች ዝዉዉርን ለማጎልበት እንዲሁም የገበያ ዕድሎችን በመፍጠር በዲጂታል ዓለም ዉስጥ ያሉ የሴት ሠዓሊያንን የጥበብ ስራዎች ተደራሽ ለማድረግ ከዩኔስኮ ጋር በትብብር ፕሮጀክን ይፋ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ የሴት የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች ብራንዳቸዉን እና የዲጂታል ስብዕና ከማጎልበት ባሻገር የባህል ምርቶች በብራንዲንግ፣ ዲጂታል አካታችነትና የንቅናቄ መፍጠሪያ መድረኮችንም ያካተተ ነዉ ተብሏል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት የገበያ ዕድሎችን ተደራሽ ማድረግ፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥበቃን እንዲሁም ፍትሃዊ ክፍያ ለጥበብ የፈጠራ ስራዎች እንዲኖሩ ዕድል የሚፈጥር ነዉም ተብሏል፡፡

20 ሴት ሠዓሊያን በዚህ ፕሮጀክት በብራንዲንግ፣ በማህበራዊ ሚዲያ አመራር፣ ድህረገጽ አጠቃቀም፣ የይዘት ዝግጅት እና የገበያ ልማት ስልቶች ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን ያገኛሉ፡፡በተጨማሪም የሠዓሊዎቹ ስራዎች በዓዉደ ርዕይ ይዘት ይቀርባሉ፡፡

የግራር የጠቢባን መናሀሪያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሴሚናስ ሀደራ ‹‹ ማንኛዉም የስነ ጥበብ ሙያተኛ በዚህ በዲጂታል ዘመን ያሉትን ዕድሎች መገንዘብ እና መጠቀም አለበት ያሉ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ በተለይ ሴት ሰዓሊያን ያላቸዉን ፈጠራ እና ተሰጥኦ ተገቢዉን ዕዉቅና እንዲያገኝ የሚያስችል ዕድል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በተጨማሪም ለ1መቶ በጥበብ እና ቴክኖሎጂ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ነዉ ተብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply