ግስላው የአማራ ልዩ ኮማንዶ በዛሬው ዕለት ተመርቆ በማየቴ ደስ ብሎኛል! ~~~~~~ አሸናፊ ገናን ~~~~~~ ጠላቶቻችንን እግር በእግር እንቅስቃሴያቸውን ለመገደብ የራስን ሃይል ማጠናከር አስ…

ግስላው የአማራ ልዩ ኮማንዶ በዛሬው ዕለት ተመርቆ በማየቴ ደስ ብሎኛል! ~~~~~~ አሸናፊ ገናን ~~~~~~ ጠላቶቻችንን እግር በእግር እንቅስቃሴያቸውን ለመገደብ የራስን ሃይል ማጠናከር አስፈላጊ ነው። የአማራ ህዝብ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ራሱን መከላከል የሚችልበት አዋጭ መንገድ ልክ እንደ # አዳኞቹ ሰልጥኖ ወትሮ ዝግጁ የሆነን ሃይል አጠናክሮ መገንባት ከቻለ ብቻ ነው። ህዝባችን ከምንም በላይ ባለፉት ዓመታት ከባድ የሆነ ሰው ሰራሺ ችግሮችን ማሳለፉ የሚታወቅ ነው። ስለሆነም የአማራ ልዮ ኮማንዶ በዚህ ደረጃ ሰልጥኖ ለህዝቡና ለሃገሩ በቆመ ጊዜ ጠላቶቻችን አሰላለፋቸውን የሚቀይሩ መሆኑ እሙን ነው። ዓለም ላይ የሃይል ሚዛን የሚለካው ሃገሮች ባለቸው ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ነው። ስለሆነም የአማራ ህዝብ እና አመራርም ከአሉታዊ አጀንዳዎች በመውጣት ለህዝባችን የሚሆነውን ነገር እንድሰሩ አበረታታለሁ። የአማራ ልዩ ሃይል ባለፉት ሁለት ዓመታት ሃገር እና ህዝብን በጀግንነት የጠበቀበት መንገድ እጅግ የሚደንቅ ነበር። በታሪክ ሺሚያው ላይ ብዙ ስውር እና ያልተገቡ ደባዎች ቢፈፀሙበትም እናት ሃገሩን በሚገባ አፅንቶ ቆይቷል። የዛሬዎች አዲኞች ደግሞ ለነባሩ ጦር ታላቅ ደጀን በመሆናቸው የግዳጅ አፈፃፀማቸውን በተለየ ሁናቴ የሚያጠናክረው መሆኑ ግልፅ ነው። ለሁሉም አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች እና መላው የአማራ ህዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ። አመራሮቻችን አንዳንድ ጊዜ እንድህ የመሬት ላይ ስራ እየሰራችሁ ስታሳዩን ልናመሰግናችሁ እንወዳለን። ህዝባችንን ከአላስፈላጊ መዘናጋት እንዲወጣና ወትሮዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ማድረግ ተፍጥሮአዊ ግደታ ነው። ስለሆነም ከጠላታችን ብዛት አንፃር የልዩ ኮማንዶው ስልጠና ተጠናክሮ ይቀጥል። ወቅቱ መሰልጠን፣መታጠቅ እና በሃሳብ አንድ መሆንን ይጠይቃል። አማራው በሃገረ መንግስቱ ህልውናውና ክብሩ ተጠብቆ እንዲኖር ካስፈለገ መውጫ መንገዱ ወታደራዊ አቅምን መገንባት ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ አማራውን በብሔር እና በሃይማኖት እያጋጩ እርስ በእርሱ እየተታኮሰ እንዲኖር በሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ የሆነ ስሜት መኖሩ ግልፅ ነው። ስለሆነም አማራ ሆይ ከጫጫታ፣ከወቀሳ እና ከትችት ወጥተህ በመሬት ስራው ላይ ተገለፅ!! ሃገር የምታተርፈው በተግባር ሰሪዎች ውጤት ነው።ስለዚህ ልክ እንደ አዳኞቹ የተግባር ስራዎች ይቅደሙ። ጥንቃቄ እና ዝግጁነት የሁሉም ነገሮች አሸናፊዎች ናቸው። © አሸናፊ ገናን ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply