ግሸን ደብረ ከርቤ 👉የግሸን አምባ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን የተሠራው በአጼ ካሌብ ዘመነ መንግሥት በ517 ዓ.ም ነው፡፡ 👉የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በአምባው የተሠራ የመጀመሪ…

ግሸን ደብረ ከርቤ 👉የግሸን አምባ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን የተሠራው በአጼ ካሌብ ዘመነ መንግሥት በ517 ዓ.ም ነው፡፡ 👉የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን በአምባው የተሠራ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን ሲኾን መስራቹም አባ ፈቃደ ክርስቶስ የተባሉ አባት ናቸው፡፡ 👉ግሸን በቅዱ ላልይበላ ዘመን በአምባው የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን መገኘቱን ተከትሎ ደብረ እግዚአብሔር በመባል ይጠራ ነበር፡፡ 👉በአጼ ይኩኖአምላክ ዘመነ መንግሥት ደብረ እግዚአብሔር ስትባል የቆየችው ግሸን በዘመኑ አምባው ከእምነት ቦታነቱ በተጨማሪ የአስተዳደር ቦታ በመኾን የነገሥታት ልጆች እንዲማሩና በዚያው እንዲኖሩ በመደረጉ ቦታው ደብረ ነገሥት በመባል ሲጠራ ቆይቷል፡፡ 👉አጼ ዘርዓ ያዕቆብ አባታቸው ያስመጡትን ግማደ መስቀል ከሲናር ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት በዚህ አምባ ከአሳረፉት በኋላ አምባው የመስቀሉ መገኛ ነው በማለት ስያሜውን ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ቀይረውታል፡፡ 👉በግሸን ደብረ ከርቤ አምስት አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ እነሱም የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እና የቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ናቸው፡፡ 👉መስከረም 21 የሚከበረው በዓል ከቅድስት ማርያም ክብረ በዓልነቱ በተጨማሪ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አሳድሰው ቅዱስ መስቀሉን በክብር ያሳረፉበት ቀን በመኾኑ በዓሉ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ

Source: Link to the Post

Leave a Reply