ግብርና ሚኒስቴር ከ2ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን ገለጸ፡፡ግብርና ሚኒስቴር በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም በሌሎች የአገራችን ክፍሎች…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/sZPU09GVOj-hod4k38FJZUzYjnHtKkF8IPBzUn88YlpCdA8KorjAB7WVXJV6B8zZJ9lps1XiNVvMY-OnTyrf5CtM3NZWGwIoHUX6rFbA3L3wyFJC4CPygtBRaKJA9ip13zAgD0q-Jy1brNbRnxebViAJUmCRZdnWG3KfHxOs40i7c4XQeXE2tESnZQuhX8pChk-DGCLDJYBBBkPQIpr6kKEn3rWuYtVDfjfzSJvwvZfc76iblLrpBqVi2tsZxI7WOX41rpAjecz0Vk64cYe_iLTRZSUCSFqI7abYl6mogIDw99vyTqaTR_vHC234m2kDgXmsi4BDYx4xh2eWYTVlVw.jpg

ግብርና ሚኒስቴር ከ2ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን ገለጸ፡፡

ግብርና ሚኒስቴር በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም በሌሎች የአገራችን ክፍሎች 3ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማረስ አቅዶ እስካሁን ድረስ ከ2ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬትን በዘር መሸፈኑን አስታዉቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በዚህ ሄክታር መሬት ላይ 120 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት አቅዶ መነሳቱን ገልጾ እስካሁን ከ50 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ገልጿል፡፡

በባህላዊ መንገድ ከ1ሚሊየን ሄክታር በላይ ያለ ምርት እንዲሁም ከ3መቶ50 ሺህ ሄክታር በላዩን ደግሞ በኮምባይነር መሰብሰቡንም ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

በ2016 ምርት ዘመን በተመሳሳይ በእነዚህ አከባቢዎች ላይ በበልግ እርሻ ከ3ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት እና ከ81 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱንም አስታዉቋል፡፡

የበልግ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለጸዉ ሚኒስቴሩ፤ ከ2ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን እና ከ8መቶ20ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑንም ነዉ የገለጸዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply