
አጭበርባሪዎች በሞቱ ሰዎች ስልክ ሳይቀር እየደወሉ ሰዎችን እያታለሉ ነው ተብሏል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ታማኝ ግብር ከፋዮችን ለማበረታታት ያዘጋጀው ሽልማት የደረሳቸው በማስመሰል አጭበርባሪዎች ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን እያታለሉ ይገኛሉ ብሏል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፣ከገቢዎች የተደወለ በማስመሰል አጭበርባሪዎች ለግብር ከፋዮች በመደወል የወንጀል ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ነው ያለው፡፡
አጭበርባሪዎቹ የግብር ከፋዮችን አድራሻ እና ማንነት በመለየት የሚፈልጉትን አገልግሎት እንደሚሰጧቸው በማግባባት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚጠይቁም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ አዲስ ይርጋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፣ የኦዲት ግኝት እንሰራላቹሃለን፣ ግብር እናስቀንስላቹሃን እያሉ አጭበርባሪዎች ግብር ከፋዩን እየበዘበዙት ይገኛሉ ብሏል፡፡
እነዚህ ግለሰቦች የሚጠቀሙባቸው ስልኮች የማን እንደሆኑ የማይታወቁ እና አንዳንዶቹ በሞቱ ሰዎች አድራሻ ጭምር በመጠቀም ከፍተኛ ግብር ከፋዩን እያጉላሉት እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
በዚህ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በየቀኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድረስ በመምጣት ቅሬታቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ ነው አቶ አዲስ ይርጋ የተናገሩት፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Source: Link to the Post