ግብጽ ለ3ሺህ እስረኞች ይቅርታ አደረገች፡፡ሀገሪቷ የኢድ አልፈጥር በአልን ምክንያት በማድረግ ለ3ሺህ ያህል እስረኞች ይቅርታ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከፈረንጆቹ 1…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/XHhBFQWUb79hDLQM-Ri1KYnb998LIWh1Hnt5hRLuLy6hri2slJq0tQOn3m0Cchqa-jGq9UcjZLOuie3UWFQ1UokZzdGjV7DlIuPcK_skWGXYMz7lYZYDrCbcc3ztdqxuxjX1AXwqmOgd7XWTCvS3uSA1B487dn5khF4RoQNixhZdpYcBqHeI7uT2uK8iJznCIofKT5qJfeVPSvBANFJH-2t2SQtPsizKURk565ChSUgHn-QY1YpxP4LM83bx6RrMwIcnIxr3V-F4fURRDkoe14qXDa5Yd7MKi_GTPddJo-djyrRIdDn7oVzZhlkpM-QjDcmb1QjgeilWrSRAS8YZzQ.jpg

ግብጽ ለ3ሺህ እስረኞች ይቅርታ አደረገች፡፡

ሀገሪቷ የኢድ አልፈጥር በአልን ምክንያት በማድረግ ለ3ሺህ ያህል እስረኞች ይቅርታ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡
ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከፈረንጆቹ 1982 አንስቶ እስር ቤት የነበሩ እስረኞች ይቅር ማለታቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ይቅርታ ከተደረላቸው እስረኞች መካከል የመንግስትን ብልሹ አሰራር አብዝቶ በመተቸት የሚታወቀዉ ጋዜጠኛ ሆሳም ሞኒስ እንደሚገኝበትም ነው የተገለጸው፡፡
ግብጽ ከአለማችን በርካታ እስረኞችን በማሰር ስሟ የሚጠቀስ ሀገር ስትሆን፣ ከኢራን በመቀጠልም ከፍተኛ እስረኞችን በማጎር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

ለፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ አስተዳደር እንቅፋት ናቸው ተብለው የሚጠሩት 41 ያህል የፖለቲካ እስረኞችም መፈታታቸው ተገልጿል፡፡
ባሁኑ ሰዓት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ60ሺህ በላይ እስረኞች እንደሚገኙም ነው የሰብአዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች ያወጡት መረጃ የሚጠቁመው፡፡

ከእስረኞቹ መካከልም አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚወስዱ የአፍሪካ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሚያዝያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply