ግብጽ እስራኤል በጋዛ ድንበር ይሰማራ ስትል ጥያቄ ያቀረበችዉን የጥምር ጦር ሃሳብ ዉድቅ አደረገች፡፡የእስራኤል እና የግብጽ ጥምር ጦር በጋዛ ሰርጥ ድንበር ላይ ይሰማራ ስትል እስራኤል ያቀረበ…

ግብጽ እስራኤል በጋዛ ድንበር ይሰማራ ስትል ጥያቄ ያቀረበችዉን የጥምር ጦር ሃሳብ ዉድቅ አደረገች፡፡

የእስራኤል እና የግብጽ ጥምር ጦር በጋዛ ሰርጥ ድንበር ላይ ይሰማራ ስትል እስራኤል ያቀረበችዉን ጥያቄ ግብጽ ዉድቅ ስለማድረጓ የእስራኤል የዜና ምንጮች እየዘገቡ ነዉ፡፡

ቦታዉ በሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት ምንም ዓይነት ጉዳይ ከመፈጸሙ በፊት ፍቃድ ሊጠየቅበት የሚገባ በመሆኑ የእስራኤል ጦር ያለምንም ፍቃድ በቅርቡ በስፍራዉ ያደረሰዉ የቦምብ ጥቃት ግብጽን ስለማስቆጣቱ ተነስቷል፡፡

የግብጽ ባለስልጣናት በእስራኤል የሚደረግ ማንኛዉም ዓይነት የወታደራዊ ዘመቻ በሲናይ ባህረገብ ላይ ቀጥታ ተጽዕኖ ይኖረዋል በሚል ከባድ ስጋት ዉስጥ ወድቀዋል ነዉ የተባለዉ፡፡ ግብጽም በስፍራዉ ምንም ዓይነት የሃማስ ዋሻዎች የሉም ስትል በተደጋጋሚ ተናግራለች፡፡

እስራኤል ለሃማስ ጥቃት በጋዛ ላይ እያደረሰች ባለችዉ የዓየር እና የምድር ድብደባ ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ ከ19ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፡፡

በሃማስ ጥቃት ደግሞ ወደ 1ሺህ 2መቶ እስራኤላዊያን የተገደሉ ሲሆን 1መቶ 30 የሚሆኑት ደግሞ ታግተዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8)

Source: Link to the Post

Leave a Reply