ግብጽ 6ሺህ የሚሆኑ ጉዳት የደረሰባቸዉን ፍልስጤማዊያንን እንድታጓጉዝ ጥያቄ ቀርቦላታል፡፡በጋዛ የሚገኝ የመንግስት ሚዲያ ግብጽ 6 ሺህ የሚሆኑ ፍልስጤማዊያን የጦርነት ተጎጂዎች የህክምና አገል…

ግብጽ 6ሺህ የሚሆኑ ጉዳት የደረሰባቸዉን ፍልስጤማዊያንን እንድታጓጉዝ ጥያቄ ቀርቦላታል፡፡

በጋዛ የሚገኝ የመንግስት ሚዲያ ግብጽ 6 ሺህ የሚሆኑ ፍልስጤማዊያን የጦርነት ተጎጂዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ከጋዛ እንድታስወጣቸዉ ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል፡፡

በጋዛ ሰርጥ እየደረሰ ያለዉን የሰብዓዊ ጉዳት ተከትሉ ግብጽ የራፋ መሻገሪያ ድንበርን በመክፈት 6 ሺህ ፍልስጤማዊያን በሌሎች አገራት በአፋጣኝ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እንድታደርግ ጥሪ አድርጓል፡፡

በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች ቁጥር ከ58ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን፤ ከእዚህ ዉስጥ 6ሺህ ፍልስጤማዊያን ጽኑ ጉዳት የደረሰባቸዉ እና 5ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ናቸዉ፡፡

ከቁጥሩ ከፍተኛ መሆን አንጻር በጋዛ የሚገኙ ሆስፒታሎች ህክምና መስጠት እንዳልቻሉም ተገልጿል፡፡

የመንግስት ሚዲያዉ ይፋ እንዳደረገው በየቀኑ ጉዳት ደርሶባቸዉ ከጋዛ የሚወጡ ዜጎች ቁጥር ከ10-20 ብቻ ነዉ ፡፡

ይሆን እንጂ በየዕለቱ የተጎጂዎች ቁጥር በመቶዎች እየጨመረ ይሄዳል ያለ ሲሆን በዚህ ምክንያት ህክምናዉን ያላገኙ ዜጎች የጉዳት እና የህመም መጠን ደግሞ ከፍ እያለ ይሄዳል ሲል ገልጿል፡፡

ግብጽም በየቀኑ 10 እና ከዚያ በላይ ሰዎችን ብቻ ከምታጓጉዝ ቁጥሩን ወደ መቶዎች እና ሺዎች ከፍ በማድረግ የብዙዎችን ህይወት ማትረፍ ትችላለች ሲል ጥሪዉን አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካ እና ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ እያደረሰች ያለችዉን የዘር ማጥፋት ጦርነት እንዲያስቆሙ ጠይቋል፡፡

93ኛ ቀኑን በያዘዉ የእስራኤል ጋዛ ጦርነት ከ22ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን የተገደሉ ሲሆን፣ከ58 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል እንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ፡፡

እስከዳር ግርማ

ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply