ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ለምታደርገው ድርድር ቱርክን እምነት እንደምትጥልባት አስታወቀች፡፡የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትናንትናዉ እለት እንዳስታወቁት ሀገራቸው ከቱርክ ጋር የነበራትን ግንኙነ…

ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ለምታደርገው ድርድር ቱርክን እምነት እንደምትጥልባት አስታወቀች፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትናንትናዉ እለት እንዳስታወቁት ሀገራቸው ከቱርክ ጋር የነበራትን ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ የምትፈልግ መሆኗን እና ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞም ከኢትዮጵያ ጋር በትጥቅ ግጭት ውስጥ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሜህ ሽክሪ ከብሉምበርግ ቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ግብፅ “ከአንካራ ጋር መደበኛ ግንኙነቷን ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ” እና ፈጣን እርምጃዎችን ለማግኘት ጓጉታ የነበረ ቢሆንም ተጨማሪ ሥራ መሰራት አለበት ብለዋል።

በቱርክ ዋና ከተማ እየተካሄደ ባለው የሁለተኛ ዙር ውይይቶች “አሁንም ውጤቱን መገምገም አለብን” ብለዋል።
ግብፅ ያልተፈቱ ጉዳዮች እንዲፈቱ ለተጨማሪ እድገት በሩ ክፍት ይሆናል ብለዋል ሽክሪ።
ቱርክ ለሙስሊም ወንድማማቾች ህብርት ድጋፍ ታደረጋለች በሚል ቅራኒ ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይባስ ብሎም ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሙርሲ በ 2013 በወታደራዊ ሀይል ከሥልጣን መውረድ ጋር ተያይዞም ግንኙነታቸው ተዳክሟል።

ቱርክ ትሪፖሊ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘውን የሊቢያ መንግሥት ስትደግፍ ፣ ግብፅ ደግሞ በምሥራቃዊው ኃያል ካሊፋ ሃፍታር የሚመራውን ትደግፋለች።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኅዳር ወር መመረጣቸውን ተከትሎ ሁለቱ አገራት በክልሉ ውስጥ ያለውን የሀይል ሚዛን ለመከፋፈል እየተገፋፉ ነው፡፡

የዓባይ ግድብን በተመለከተም ከኢትዮጵያ ጋር በተፈጠረው ውጥረት ላይ ግብፅ ለድርድር ቁርጠኛ መሆኗን እና ከማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ግጭት ለመራቅ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።
የግብፅ ባለሥልጣናት ቀደም ሲል ሁሉም አማራጮች ክፍት እንደሆኑ ተናግረው ነበር ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

እንዲሁም የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤልሲሲ የውሃ ድርሻ ለሀገራቸው የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ መሆኑን እና ሊታለፍ የማይችል “ቀይ መስመር” ነው ሲሉ መደመጣቸውን አናዶሉ ዘግቧል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ጳጉሜ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply