ግብፅ የጉምዝ ታጣቂ ሀይሎችን  እንደምትደግፍ የስለላ መረጃዎች እንደተገኙ የቱርኩ የዜና ወኪል አናዶሉ ዘገበ፡፡  (አሻራ ጥር 16፣ 2013 ዓ.ም)  የቱርኩ ዋነኛ የዜና ወኪል  አናዶሉ  ባ…

ግብፅ የጉምዝ ታጣቂ ሀይሎችን እንደምትደግፍ የስለላ መረጃዎች እንደተገኙ የቱርኩ የዜና ወኪል አናዶሉ ዘገበ፡፡ (አሻራ ጥር 16፣ 2013 ዓ.ም) የቱርኩ ዋነኛ የዜና ወኪል አናዶሉ ባ…

ግብፅ የጉምዝ ታጣቂ ሀይሎችን እንደምትደግፍ የስለላ መረጃዎች እንደተገኙ የቱርኩ የዜና ወኪል አናዶሉ ዘገበ፡፡ (አሻራ ጥር 16፣ 2013 ዓ.ም) የቱርኩ ዋነኛ የዜና ወኪል አናዶሉ ባጠነቀረው ዝርዝር ዘገባ መሰረት ግብፅ በሱዳን በኩል የጉምዝ ታጣቂዎችን ማስታጠቋን ይፋ አድርጓል፡፡ መተከልን የብጥብጥ ማዕከል በማድረግ ግድቡን የራስ ማድረግ በሚል የፖለቲካ ስሌት ጉባ ወረዳን በጉምዝ ታጣቂዎች ያስያዘች ሲሆን፣ አንዳንድ የጉምዝ አመራሮችም መኖሪያቸውን በሱዳን ብሉናይል ግዛት አድርገዋል፡፡… ግብፅ ያኮረፉ ሀይሎችን በማደራጀት ቢሻንጉል ጉምዝ ሙሉ በሙሉ የሱዳን ነው እንዲሉም እየሰራች ትገኛለች ተብሏል ፡፡ አናዶሉ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ግብፅ ደቡብ ሱዳንን የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ነፃ ቦታ እንዲሰጣቸው ማግባባቷንም ዘግቧል፡፡ ደቡብ ሱዳን ግን ከኢትዮጵያ ወዳጅ ስለሆንኩ ኢትዮጵያን የሚወጋ ሀይል በጁባ አላሰለጥንም እንዳለች አናዶሉ በስፋት ዘግቧል፡፡ ግብፅ ኢትየዮጵያን ለማተራመስ ሱዳን እየተጠቀመች ሲሆን፣ በዋነኛነት ግን የሀገር ውስጥ ታጣቂዎች የግብፅ ወኪል እንደሆኑ አናዶሉ አስነብቧል፡፡ የመተከሉ ከጉምዝ ባለፈ ኦነግ ዋነኛ ተዋናይ ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማውም በሀገር ውስጥ የግዛት ማስፋፋት እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ መተከልን እርስ በእርስ ጦርነት ማዕከል ሲሆን ግድቡ ይረሳል፡፡ ኢትዮጵያም ልማቱን ትረሳለች፡፡ ይህን ግብፅ በስኬት ወስዳዋለች፡፡ በሌላ በኩል አቶ ደመቀ መኮንን ትናንትና የመተከል ተፈናቃዮችን የጠየቁ ሲሆን፣ እንዲታጠቁ እና ከቦታቸው እንዲመለሱ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ሀገርም የጋራ ነው፡፡ መጤ የሚባል የለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ነገር ግን የመተከል ችግር መዋቅራዊ ሆኖ ስለተሰራ የአመራር አመዳደብ እና የህግ መሰረታዊ ማሻሻያ ካልተደረገ መተከል የንፁሃን ጭፍጨፋ እና የውጭ ሀይሎች የፖለቲካ ሜዳ መሆኑ አይቀርም፡፡ በመተከል ሁለት ሺ ያህል ሰዎች ፍርድቤት ሳይቀርቡ ለሁለት ዓመት የታሰሩ ሲሆን፣ ከ 600 በላዮ በዚህ ሳምንት በዋስ ተለቀዋል፡፡ በመተከል ያለው የመንግስት መዋቅር ሁለት ዓመት ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ያስራል፡፡ ያስጨፈጭፋል፡፡ ያፈናቅላል፡፡ ህዝብን በመጤ እና በነባርነት እየመደበ ለገዳዮች ሽፋን ይሰጣል፡፡ ይህን የመሰለው የበሰበሰ የመንግስት መዋቅር እና ስራዓት በመሰረታዊነት ካልተቀየረ፣ ተጠያቂነት ካልሰፈነ በመተከል ያለው ሁኔታ አስቸጋሪነቱ ሊቀጥል ይችላል፡፡ በመተከል ከ200ሺ ሰዎች በላይ ተፈናቅለው እስካሁን አልተመለሱም፡፡ ግድያ እና መፈናቀሉም አንፃራዊ መሻሻል ቢኖርም፣ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፣ በመተከል መሰረታዊ ለውጥ አልመጣም፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply