ግዕዝ ባንክ በድጋሚ የአክስዮን ሽያጭ መጀመሩን ገለጸ፡፡በምስረታ ሂደት ላይ የሚገኘዉ ግዕዝ ባንክ አ.ማ የባንክ ኢንዱስትሪዉን ለመቀላቀል ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለመስረታ ሂደት የሚያ…

ግዕዝ ባንክ በድጋሚ የአክስዮን ሽያጭ መጀመሩን ገለጸ፡፡

በምስረታ ሂደት ላይ የሚገኘዉ ግዕዝ ባንክ አ.ማ የባንክ ኢንዱስትሪዉን ለመቀላቀል ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለመስረታ ሂደት የሚያበቃዉን የአክስዮን ሽያጭ እያከናወነ መቆየቱ ተገልጿል።

ባንኩ ባስቀመጠዉ እቅድ መሰረት በህዳር 2013 ዓ.ም የአክስዮን ሽያጭ የሚያበቀታበት አድርጎ እየሰራ የነበረ ቢሆንም በሃገራችን በተፈጠረዉ ወቅታዊ ችግር ምክንያት እንቅስቃሴዎች ተገተዉ እቅዶቻቸዉን ማሳካት አለመቻሉ የአዳዲስ የአክስዮን ሽያጭ ሊዘገይ እንደቻለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በሀገሪቱ የመጣዉ የሰላም ስምምነትን ምክንያት በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመነጋገር በድጋሚ የአክስዮን ሽያጭ መጀመራቸዉን የግዕዝ ባንክ አደራጅ ኮሚቴ አባል አቶ ቶማስ ሃይለ አሳዉቀዋል።

በዚህም መሰረት በምስረታዉ ሂደት ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ በመላዉ ሀገሪቱ በተከፈቱ የዝግ እና የአገልግሎት ሂሳብ ቁጥሮች በኩል የግዕዝ ባንክ አ/ማ የመመስረቻ የአክስዮን ሽያጭ ግዢ ከ50.000 ብር በላይ መክፈል ይጠበቅባታል ተብሏል።

የመስራች የአክስዮን ሽያጭ የአንድ አክስዮን መጠን 1000 ብር ሲሆን መስራች አባል ለመሆን 50 አክስዮኖችና ከዚያ በላይ መግዛት ወይም ከ50ሺህ ብር በላይ መክፈል ይጠበቅባታል።
የአክስዮን ሽያጭ በተመለከተ ግማሽ ቢሊዮን ብር በአንድ ወር ግዜ ዉስጥ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዛቸዉን የግዕዝ ባንክ አደራጅ ኮሚቴ አባል አቶ ቶማስ ሃይለ ገልፀዋል።

የአከፋፈል ስርዓቱም ሁለት ዓይነት ነዉ የተባለ ሲሆን የመጀመሪያዉ ሙሉ ክፍያዉ መክፈል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቅድሚያ 25 በመቶ ከፍሎ 75 በመቶ እስከ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ቆጥበዉ መግዛት እንደሚችሉ ተነግሯል።

በአቤል ደጀኔ

መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply