
የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሚደርሰው ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀላጠፍ በሚል ከሐሙስ መጋቢት 15/2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚጸና ግጭት የማቆም ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል። ህወሓትም የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ በአስቸኳይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እንደሚስማማ ገልጿል። ይህ ስምምነት እርዳታ እንዲቀርብ ከማስቻሉ ባሻገር በጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች በኩል ግጭቱን ለማብቃት የውይይት ዕድልን ሊከፍት ይችላል የሚል ተስፋን ፈጥሯል።
Source: Link to the Post