ግፈኛው የህወሀት ቡድን በመከላከያ ሰራዊትና የትግራይ ህዝብ ወንድም በሆነው በአማራ ህዝብ ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ የፈፀመውን ክህደት የተሞላበት ጦርነት በፅኑ እንደሚያወግዘው የመላው ኢት…

ግፈኛው የህወሀት ቡድን በመከላከያ ሰራዊትና የትግራይ ህዝብ ወንድም በሆነው በአማራ ህዝብ ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ የፈፀመውን ክህደት የተሞላበት ጦርነት በፅኑ እንደሚያወግዘው የመላው ኢት…

ግፈኛው የህወሀት ቡድን በመከላከያ ሰራዊትና የትግራይ ህዝብ ወንድም በሆነው በአማራ ህዝብ ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ የፈፀመውን ክህደት የተሞላበት ጦርነት በፅኑ እንደሚያወግዘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ በወቅታዊ ጉዳይ ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ግፈኛው ህወሀት በመከላከያ ሰራዊትና የትግራይ ህዝብ ወንድም በሆነው በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ጥቃት በፅኑ አውግዟል። ህወሀት የመከላከያ ሰራዊቱ ለረዥም ዓመታት ከጠላት ለመከላከል ለከፈለው መስዋዕትነት ክብርና ምስጋና መቸር ሲገባው ጨለማን ተገን በማድረግ የፈፀመው ጥቃት ክህደትና ዝርፊያ ስለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘበው ይገባልም ብሏል መኢአድ በመግለጫው። የመከላከያ ሰራዊቱ በትግራይ አካባቢ ለረዥም ዓመታት የቆየው ለቅንጦት ሳይሆን ድንበርና ህዝብን ከጠላት ለመከላከል እንደሆነ ለትግራይ ህዝብ የሚሰወር ጉዳይ አይደለምም ብሏል። ነገር ግን አባቶቻችን እንደሚሉት “ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይተውም” እንደሚባለው ህወሀት በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመው ተደራራቢ ጥቃት አልበቃው ሲል የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በሚያስከብረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ይህን የወንጀል ድርጊት መፈፀማቸው በ1969 በሶማሊያ ወረራ ወቅት የፈፀሙትን ሀገራዊ ክህደት ያስተውሰናል ብሏል። መኢአድ ሲቀጥል ህወሀት የራሱን የማይገባ ጥቅምና ፍላጎት ለማሳካት ሲል ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በፍቅር የሚኖረውን የትግራይ ህዝብ ለመነጠል እየሄደበት ያለው ተግባር ተቀባይነት የለውም ብሏል። እንደማሳያም በዛሬው እለትም በዳንሻ አካባቢ በአማራ ላይ የከፈተውን ተኩስ ያስታወሰው መኢአድ መላው ኢትዮጵያዊያን ሀገርን ለማዳንና ሰላምን ለማስከበር እየተንቀሳቀሰ ካለው ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲሰለፉ ሲል ነው ጥሪ ያቀረበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply