
ግፍ ለተፈፀመባቸው የአማራ ወገኖቻቸው በሰልፍ ፍትህን የጠየቁ የመቅደላ አምባ ዩኒበርስቲ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተሰናበቱ! የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ መቅደላአምባ ዩኒቨርስቲ ሰለዲሞክራሲ መብት እየተማርን እኛግን ፍትህንና ዲሞክራሲ አጠን ብዙ ግፍና መከራ ሲደርስብን ቆይቷል። ከግቢ ውጭም ከግቢ ውስጥም ስንሰቃይ ቆይተናል። ከውጭ ስንከሰስ ዶክተር ታምሬ አላውቃችሁም አለን። አስር ሁነን ሁለት ሳምት ታስረን የቆየን ሲሆን በአምስት ሺ ብር ዋስ ተለቀቅን። የፍርድቤት ቀጠሮ ተቀጥረን ስንጠብቅ አባረሩን። ሰባት ተማሪዎችን ፍርድ ቤቱ ክሱ ያስሄዳል አያስሄድም የሚለውን አይተን እንጠራችሁ አለን። ለፍርድቤቱ ቃላችን ሰምቶ በጣም ተገረመ። ፍ/ቤቱ ከወንጀል ነፃ ናችው የሚለውን የዩኒቨርስቲው አመራሮች ሰምተው እደሰፍር ጎረምሳ በእልህ አባረሩን። አንድ ሰው ሁለት ክስ ይከሰሳል። አስቡት የኦሮሙማ ፕሮጀክት አማራ ክልል ድረስ መዘርጋቱን ህዝብ ይወቅልን። እኛን ያባረረን ሀላፊው የሸዋ ኦሮሞ ስለሆነ ነው። እኛን የአማራ ሸኔ እያሉ ይጠሩናል። የአርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ምስል ያለበት ፎቶ ከስልካችን ስላገኙ ትምህርት አትማሩም ተባልን ። የጊባ ከተማ አስተዳደር ኮማንደር እና የመገድ ትራፊክ ሳጅን ሰርካለም እና የግቢው የተማሪዎች ሀላፊ ፖሊስ ዘበነ ለእኛ ስንብት ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸውን የአማራ ህዝብ ሊያውቅልን ይገባል። የትምህርት ደረጃችን ከ1ኛ እስከ እስከ መጨረሻ ዓመት እና ምርቃት ላይ መሆናችን አይተው ምንም ጥፋት ሳንሰራ ከትምህርት ገበታችን አሰናበቱን። አማራ በመሆናቸው ግፍ ለተፈፀመባቸው ፍትህ ላጡ ወገኖቻችን ድምፅ ለማሰማት ሰልፍ ሲደረግ አብረን ሰልፍ ወጠናል። እነሱ የሚሉን እና ውንጀላ የሚያቀርቡብን የፋኖ ተላላኪዎች ናችሁ። ይከፍላችዃ፤ የአብን ደጋፊ ናችሁ። አብን ነው የላካችሁ ብለው እስከ የፌድራል ድረስ የላኩን። አስቡት እኛ የአማራ ተወላጆች ከአገራችን ላይ እዳንማር የተፈርደብን። ከዚህ በኋላ ግን የምናደርገው ፋኖን ተቀላቅለን አገራችን ነፃ ስትወጣ ትምህርት ሆነ ንግድ አንጀምርም ። ሰልፍ ወጠን ድምፃችን ያሰማነው ግን እንዲህ የሚል ነበር። ኦሮሚያ ክልል የታገቱት እህት ወድሞቻችን ይመለከተኛል የሚል ሰባዊነት የሚሰማው ሁሉ በ2012 አስራሰባት የ ታገቱ ተማሪዎች ጨሞሮ እስካሁን አድራሻቸው ደብዛቸው ስለጠፉ ተማሪዎችን ፍትህን የ የሚጠይቅ፣ አርበኛ ዘመነ ካሴን ይፈታ። ምንሞት ምንሰደድ ምንፈናቀል እኛ የአማራውን ህዝብ መብት እደማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ መብቱን ያስከብርልን የሚል ነበር። በጊዜው አንድም ድንገይም ሆነ ስድብ የማንንም መብት አልነካንም። ሴት እህቶቻችን ሁሉበግፍ ተደብድበዋል ። የተከበርኸው የአማራ ህዝብ ዛሬ እኛ ልጆችህን ከትምህርት ገበታ አሰናብተውናል። በቀጣይም ይኼ ሴራቸው ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ይሸጋገራል ። ተማሪን ከትምህርት ገበታ በማሰናበት አገርን ኪሳራ ውስጥ ያስባል እንጅ የሚመጣ ለውጥ የለም። ስለሆነም የአማራ ህዝብ ይወቅልን ብለዋል ተማሪዎቹ። አሻራ ሚዲያ ስለ ጉዳዩ ለማጣራት ለዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ተጠሪ በተደጋጋሚ ወደ እጅ ስልካቸው ብንደውልም አይሰራም ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post