ጎንደር በጥምቀት በዓል እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን ዝግጅት ማድረጓ ተገለፀ። ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በጥምቀት በዓል እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖ…

ጎንደር በጥምቀት በዓል እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን ዝግጅት ማድረጓ ተገለፀ። ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በጥምቀት በዓል እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገልጧል፡፡ የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ ቻላቸው ዳኜው እንደገለፁት በጥምቀት በዓል ወቅት ከ750 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ጎብኚ ወደ ጎንደር እንደሚመጣ ይጠበቃል። ለዚህም ከ400 በላይ ሆቴሎች እና ድንኳን የሚጣልባቸው ሥፍራዎች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ እንደ እንግዶች አቅም የማረፊያ፣ የምግብና መጠጥ መሸመቻ አማራጭ መሰናዳቱንም አስገንዝበዋል። በሰሞነ ጥምቀት እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝም ምክንያት ለኢኮኖሚው ገቢ እንደሚያገኝ ጠቁመዋል። ከ400 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ጥምቀተ ባሕርና የታቦታት ማደሪያ ሥፍራ መኖር ጥምቀትን በጎንደር ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል። ይህም በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሣይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በፈረንጆቹ 1978 መመዝገቡን አስታውሰዋል። በባህል ሣምንት፥ የአካባቢውን ብሎም የክልሉን ባህል፣ ወግና ትውፊት የሚያሳዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት የአዝማሪ ፌስቲቫል መኖሩን አቶ ቻላቸዉ ገልፃዋል። በባህል ሣምንት ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ሀገራዊ አንድነትን በሚያፀና ሁኔታ እንደሚከበር አመላክተዋል። ዘገባው የጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply