ጎንደር ከተማ በአንድ ግለሰብ በትግል ላይ እያሉ ለተሰው አርበኞች የ170 ሽህ ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ተደረገ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አ…

ጎንደር ከተማ በአንድ ግለሰብ በትግል ላይ እያሉ ለተሰው አርበኞች የ170 ሽህ ብር የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ተደረገ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አቶ አህመድ ኑር የጎንደር ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ የወራሪውን የትህነግ ኃይል ለመመከት በትግል ላይ እያሉ ለተሰው አርበኞች ቤተሰቦች የ170 ሽ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በሀገርና ህዝብ ብለው በትግል ላይ እያሉ ለተሰው የአርበኛ ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለሌሎች አርዓያ ሆኖ ለመገኘት ድጋፉን ማድረግ መቻሉን አህመድ ኑር ገልፀዋል፡፡ ድገፍ ከተደረገላቸው የአርበኛ ቤተሰቦች መካከል ወይዘሮ ሰልካለም ቦጋለ አንዷ ነች፡፡ ባለቤቷ የአርበኝነት ገድል እየሰራ ህይወቱ ቢያልፍም ጓደኞቹ እያደረጉልኝ ያለው ድጋፍ ግን ከፍ ያለ ነው ብላለች፡፡ አሁን ድጋፍ ያደረጉትን ግለሰብ አቶ አህመድ ኑርና እገዛ ላደረጉ ሌሎች ግለሰቦቸም ምስጋና አቅርባለች፡፡ የአርበኛ ቻላቸው እንዬው ወንድም አርበኛ ገበየሁ እንዬው ደግሞ ወንድሜ ለዓለማው በመሞቱ ቁጭት የለኝም ብለዋል። አቶ አህመድ ኑርና ሌሎች ሰዎች ለቤተሰቦቹ እያደረጉት ላለው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ድጋፉን እያስተባበረ ያለው አክቲቪስት ሰለሞን ቦጋለ ደግሞ እነዚህ አርበኞች ለእኛ ሲሉ የተሰው ጀግኖቻችን ናቸው፤ ስለዚህ ቤተሰቦቻቸው የሚደረገው ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡ አህመድ ኑር 140ሽ ብር ለአርበኛ ቤተሰቦች በየቤታቸው እየተገኙ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን 30ሽ ብር ደግሞ ዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ ለተሰው አርበኛ ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚያደርጉም በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል ሲል ጎንደር ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው ዘገበው። ክብር ለሕልውና ስትሉ ውድ ሕይወታችሁን በመክፈል በደምና አጥንታችሁ ደማቅ ታሪክ እየጻፋችሁ ላላችሁ ጀግኖቻችን በሙሉ ይሁን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply