ጎንደር ከተማ ከመገጭ የግድብ ፕሮጀክት የንጹሕ መጠጥ ውሃ እንድታገኝ የሚያስችል የዲዛይን ሥራ ስምምነት ተፈረመ

ጎንደር ከተማ ከመገጭ የግድብ ፕሮጀክት የንጹሕ መጠጥ ውሃ እንድታገኝ የሚያስችል የዲዛይን ሥራ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጎንደር ከተማ ከመገጭ የግድብ ፕሮጀክት የንጹሕ መጠጥ ውሃ እንድታገኝ የሚያስችል የዲዛይን ሥራ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ በአማራ ዲዛይን ቁጥጥር ኮርፖሬሽን እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር መካከል ሲሆን 21 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡
በስምምነቱ መሠረት የግድብ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ከሚይዘው ውሃ 30 በመቶው ለከተማዋ ነዋሪዎች የንጹሕ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ይውላል ነው የተባለው፡፡
ይህም በንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ያለውን ችግር ለመቀነስ የሚያስችል የ32 ሚሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ እንዲኖር ያደርጋልም ተብሏል፡፡
ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የተመደበለት ግድቡ በመጭው ነሐሴ ወር ውሃ መያዝ እንደሚጀምርም በስምምነት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ ተናግረዋል፡፡
በዮርዳኖስ አበበ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ጎንደር ከተማ ከመገጭ የግድብ ፕሮጀክት የንጹሕ መጠጥ ውሃ እንድታገኝ የሚያስችል የዲዛይን ሥራ ስምምነት ተፈረመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply