ጎንደር ዩኒቨርስቲ “ደማችን ለወገናችን” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሀ ግብርን ማስተባበር ጀመረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

ጎንደር ዩኒቨርስቲ “ደማችን ለወገናችን” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሀ ግብርን ማስተባበር ጀመረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጎንደር ዩኒቨርስቲ “ደማችን ለወገናችን”በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሀ ግብርን ማስተባበርን ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓም መጀመሩን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደ ወይን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል። “ልገሳው በዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ተጀምሮ በስፋት እየተካሄደ ይገኛል።” ሲሉ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ጥሪውን አክብረው ለተገኙ የዩኒቨርሲቲውን ማሕበረሰብ አባላትና ለጎንደር ወጣቶች ከልብ አመስግነዋል። ዶ/ር አስራት አፀደ ወይን “ደም በመለገሳችን የምናጎለው አንዳች ነገር የሌለ ሲሆን የምናተርፈው ግን እልፍ አእላፋትን ነው።” ሲሉም አስፍረዋል። የደም ልገሳ መርሀ ግብሩ በተለያዩ አካባቢዎች ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply