ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሴቶች እና ህጻናት የወደፊት ተስፋን እያጨለመ ይገኛል ተባለ።በኢትዮጵያ ከ140 በላይ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መኖራቸውም ተነግሯል።የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒ…

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሴቶች እና ህጻናት የወደፊት ተስፋን እያጨለመ ይገኛል ተባለ።

በኢትዮጵያ ከ140 በላይ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መኖራቸውም ተነግሯል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሙድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሴቶችና ህጻናት የወደፊት እድልና ተስፋቸው ከማጨለም ባለፈ በሁሉም ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት እየገታ ይገኛል ብለዋል።

በሀገሪቱ ከ140 በላይ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መኖራቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ በዚህም ሳቢያ በሴቶችና ህጻናት ላይ ተደራራቢና የተወሳሰበ ችግር ሲከሰት መቆየቱን አብራርተዋል።

በሴቶች ላይ እየደረሱ ከሚገኙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መካከል እንደ የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለ እድሜ ጋብቻ ዋነኞቹ መሆናቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ድርጊቶች በሴቶች ላይ አካላዊ፣ስነ ልቦናዊ እንዲሁም ማህበራዊ ቀውሶችን በማስከተል በሃገር ላይም የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

በጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡ ሴቶች መኖራቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ ድርጊቱ የሰዎችን ሰብአዊ መብት ከመጋፋት ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳጣ ይገኛል ብለዋል።

መንግስት በዘርፉ የሚያጋጥመውን ችግር ለመከላከል የተለያዩ ዓለም አቀፍ፣አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ህጎች ፖሊሲዎች ቀርጾ በመተግበር ላይ እንደሚገኝም አስታውሰዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply