ጎጆ ብሪጅ ሐዉሲንግ 105 ቤቶችን ለባለእድለኞች ለማስተላለፍ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት አካሂዷል።በአዲስ አበባ የሚታየዉን የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለመቅረፍ እየተጋሁ እገኛለዉ ያለዉ ጎጆ የመጀመ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/DUC50mHuNeymlAP6RDA40c0-WOouHVr_FWRVj0BX2Je6387OrWZNWb33_dI5kVkAUUsIGB6HXIUj11dsmRFzAgU4D9pFe28qR4Se-2RN40DTK7OFagzWMJbnRl35HlNI0UtHy4xrI1LmzW3hm97YYiY8PlBxClHluKVBOYItr75FJbHSvUEcx7v6zeWTS01yJBMl80ExuhbtP85Cd95DjFCTnW67Xlsm0d5nR5BPnUiG4gbhjFCBTzw6OasRZI0wayjkTmkEV-IGb-eCxYvKCTGyePRvOGSZeVhCywW7V1Dy2a5XBkC6ACnoHuyYFmMglgmN5XIFvjGTLvrOGvXk_A.jpg

ጎጆ ብሪጅ ሐዉሲንግ 105 ቤቶችን ለባለእድለኞች ለማስተላለፍ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት አካሂዷል።

በአዲስ አበባ የሚታየዉን የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለመቅረፍ እየተጋሁ እገኛለዉ ያለዉ ጎጆ የመጀመሪያ ዙር እጣዉን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር አዉጥቷል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አልማዉ ጋሪ እስከ መስከረም 06 2015 የተመዘገቡ 8127 ተመዝጋቢዎች በእጣ አወጣጡ ስነ-ስርዓት ተሳታፊ ሆነዋል ብለዋል፝።

ቤቶቹ ብሔረፅጌ አካባቢ ባለ ሳይት 42 እና አያት መቄዶንያ ሳይት 63 በአጠቃላይ 105 ቤቶችን ለባለ እድለኞች እጣ አውጥቷል።

በቀጣይ በሌሎች አካባቢ ሳይቶችም ግንባታ ለመጀመር እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የገለፀዉ ጎጆ ብሪጅ የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በበለፀገ መተግበሪያ በገለልተኝነት እንዳወጣም ተነግሯል።

በተለያዩ ሳይቶች የገጠሙ እክሎች እየተፈቱ በቅርቡም ግንባታ የሚጀመርባቸዉ ሳይቶች መኖራቸዉንም አቶ አልማዉ ጋሪ አስታዉቀዋል።

በአብዱሰላም አንሳር
ጥር 03 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply