
ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ በይፋ ተመሰረተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ የተሰኘ ፓርቲ መጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል የምስረታ መርሃ ግብሩን አከናውኗል። ፓርቲው ከ572 በላይ የሆኑ የጉራጌ ተወላጆች የተሰባሰቡበት ሲሆን የጉራጌን ህዝብ መብት፣ጥቅም እና ፍላጎትን ለማስከበር መመስረቱ ተሰምቷል። ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የፓርቲ ማደራጃ ፈቃድ ወስዶ ለሃገራዊ ፓርቲነት የሚያበቁ ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ላይ መቆየቱን የጊዜአዊ አደራጅ ኮሚቴ ማስታወቁ ይታወሳል።
Source: Link to the Post