ጠላትን ለመደምሰስ ልዩ ኀይልና መከላከያን እንደሚቀላቀሉ የገንዳ ውኃ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራ…

ጠላትን ለመደምሰስ ልዩ ኀይልና መከላከያን እንደሚቀላቀሉ የገንዳ ውኃ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ የአማራ ምሁራን መማክርት ከከተማው ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መክረዋል። ኢትዮጵያ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል መደፈሯ ያስቆጣት ወጣት ገነት እሸቴ ልዩ ኀይልን በመቀላቀል ጠላትን ለመደምሰስና ሀገሯን ነጻ ለማውጣት ቁርጠኛ መሆኗን ነው የገለጸችው። ለአሚኮ አስተያየቱን የሰጠው ሌላኛው ወጣት ቻሌ ገብሬ በልዩ ኀይል መመዝገቡን ገልጾ ሊገል የመጣን ጠላት በወሬ ሳይሆን ግንባር በመዝመት መፋለም እንደሚፈልግ ነው የተናገረው። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መዝመት በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ ገብተው ለመፋለም ሞራል እንደሆናቸው የገለጹት ወጣቶቹ በየትኛውም ጊዜ በየትኛውም ቦታ ጀብዱ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሀገርን ሕልውናና የዜጎችን ነጻነት ለማስከበር ጀብዱ እየፈጸመ ለሚገኘው የወገን ጦር አስፈላጊውን ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለጹት ወጣቶቹ አካባቢያቸውን በንቃት እየጠበቁ መሆኑንም ነው የተናገሩት። የሕልውና ዘመቻውን ለመደገፍ በምክክር መድረኩ የተገኙት የአማራ ምሁራን መማክርት አባልና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ገብሬ ሙሉዓለም አሁን ላይ ወጣቱ መደራጀት፣ መሰልጠን፣ መከላከያንና ልዩ ኀይልን መቀላቀል፣ መረጃ መስጠት፣ አካባቢን በንቃት መጠበቅ እና ግንባር ዘምቶ ጠላትን መደምሰስ እንዳለበት አስገንዝበዋል። ፕሮፌሰሩ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በሀገሪቱ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በማስረዳት ሀገራዊ ኀላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል። በመድረኩ የተገኙት የገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ይግለጥ አበባው ሕዝባዊ ማዕበል ፈጥሮ የመጣውን አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ቡድን ተገቢውን ምላሽ መስጠት የሚቻለው ሕዝባዊ ማእበል ፈጥሮ ግንባር መዝመት ሲቻል እንደሆነም ተናግረዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply