You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ  ለመከላከያ መኮነኖች የተናገሩት ሐሳብ ።    ባህርዳር ። ሚያዚያ 07/2014/ዓ.ም          አሻራ ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለመከላከያ መኮነኖች የተናገሩት ሐሳብ ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 07/2014/ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ለመከላከያ መኮነኖች የተናገሩት ሐሳብ ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 07/2014/ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካድሬ እያጠፋ መከላከያ ዋጋ መክፈል የለበትም ብለዋል። ታጣቂዎችም ትጥቅ ይፈታሉ ብለዋል። መረጃውን በዝርዝር እንመልከተው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ህዝብ የሚፈልገውን በመናገር ኢትዮጵያዊዉ ሙሴ፣ አሻጋሪያችን፣ አንድ ጤነኛ መሪ መቶ ሚሊየን እብዶችን እየመራ የሚሉ ውዳሴዎች አግኝተዋል። አስረን አናጣራም፣ አጣርተን እናስራለን። ኢትዮጲያዊ በየትም ቦታ ይኖራል። ኢትዮጵያ ጭቆና በቃት በሚሉ የስልጣን መባቻ ንግግራቸው ብዙዎችን አስጨብጭበዋል። በትናንትናው ዕለትም የመከላከያ መኮነኖችን ሰብስበው መቶ ከመቶ በሁለት ዓመት ውስጥ ስንዴ ለራሳችን ተርፈን ወደ ውጭ እንልካለን ሲሉ ነግረዋቸዋል። የመከላከያ ጀኔራሎችን ስለግብርና ምርት እቅድ መናገሩ የቱን ያህል አስፈላጊ ነው የሚለውን እንተወዉና፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ወደ 80 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ታስገባለች። ወደ 50 ቢሊየን ብርም በስንዴ ብቻ ወጭ ይደረጋል። ይሄ ሁሉ ባለበት ለስንዴ ራስን መቻል መናገራቸው ቢያስጨበጭብ ችግር አልነበረውም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2012 ዓም በሸህ ሁሴን አላሙዲ የተገነባው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በአዲስ አበባ ሲመረቅ ከሁለት ዓመት በሗላ ስንዴ ከውጭ አናስገባም ብለው ነበር። ሁለት ዓመቱ ሲደርስ እንደገና ከሁለት ዓመት በሗላ ስንዴ ወደ ውጭ እንልክ ካልሆነ በስተቀር ወደ ውስጥ አናስገባም አሉ። የዓለም የምግብ ምግብ ፕሮግራም ሰሞነኛ ትንታኔው ኢትዮጵያ በስንዴ እጦት ርሃብ ከሚያስተናግዱ ሀገራት ተርታ ትቀመጣለች የሚል ነው። ኢትዮጵያ 30 ከመቶ ስንዴ የምታመጣው ከዮክሬን ነበር። ዮክሬን ጦርነት ውስጥ ስትገባ የስንዴ አቅርቦት ጠፋ። በጠቅላይሚኒስትሩ ዕቅድ ቢሆን ዘንድሮ በስንዴ ራሳችን እንችል ነበር። ነገሩ በስንዴ ራሳችን ስለመቻሉ ይቆየንና ፣ ስንዴ አምራች አርሶአደሮች የአፈር ማዳበሪያ ያገኙት 40 ከመቶ አይሆኑም። ያም በተጋነነ ዋጋ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አበባ ከመትከል፣ ቤተመንግስት ከማደስ እና ሌሎች አብረቅራቂ ነገሮችን ከማሳየት ውጭ የግብርና ቴክኖሎጂ፣ የመስኖ ግድብ፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ ሰላምን አስጠብቆ ትርፍ ምርት ስለማምረት የሰሩት ስራ አይታይም። ይሄ ካልሆነ ደግሞ በምግብ ራስን መቻል በምኞት እና በጓሮ ተክል በመትከል አይረጋገጥም። ሌላው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት መሰረታዊ ጉዳይ የሀገር መከላከያ የብልፅግና ወይም በጥቅሉ የፓርቲ እስረኛ መሆን እንደሌለበት ነው። የሀገር መከላከያ የሀገር የመጨረሻው ምሽግ እና ውግንናውም ለሀገር እንጂ ለፓርቲ መሆን የለበትም ብለዋል። በብሄር ቋጥሮ ውስጥ በመግባት ከሀገር ዝቅ ማለት ለመከላላከያ አይመጥንም ያሉ ሲሆን፣ መከላከያ ለካድሬ መላላክ የለበትም ብለዋል። ካድሬ ባጠፋው መከላከያ ለማስተካከል ዋጋ ይከፍላልም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካድሬነትን አጣጥለው መከላከያን አወድሰዋል። በ2012 ዓም ለብልፅግና ፓርቲ ማደራጃ ገንዘብ በሸራቴን አዲስ ሲሰበሰብ የተማረ ኢኮኖሚ ፕሮፌሰር ቤት ወይም መኪና የለውም። እናንተ ግን ባለሀብቶች ሳትማሩ ሀብታም ሆናችሗል። ከተማረ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ያልተማረ ሀብታም ለሀገር የተሻለ ስለመሆኑ ተናግረው ነበር። ጠቅላይሚኒስትር አብይ እንደ መድረኩ ሁኔታ እንጂ መርህ የተከተለ እና ቀጣይነት ያለው ንግግር ሲያደርጉ ብዙ አይስተዋሉም። በብሄር መሸጎጥ ልክ አይደለም ቢሉም ብልፅግና በተለይም የኦሮሞ ብሌፅግና ህወሃትን ለመተካት መሮጡ የአደባባይ ሀቅ ነው። ብሄርተኛነት በብልፅግና ውስጥ ባይኖር አዲስአበባ በሙያው ፣ በህዝብ ተቀባይነቱ እና የከተማ የመምራት ልምድ ባለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትመራ ነበር። በብልፅግና ውስጥ ብሄርተኝነት ባይኖር የኦሮሞ ብልፅግና የአማራ ብልፅግናን ተቃርኖ መግለጫ አያወጣም ነቀር። የብልፅግና ሊቀመንበር ደግሞ አብይ አህመድ ናቸው። የማይግባቡ የፓርቲ ቅርንጫፎች መሪ ሆነው ከብሄር ቋጠሮ እንውጣ ብለው መምከራቸው ከራሳቸው ሁኔታ፣ ከብልፅግና መንግስት ፖለቲካዊ አረዳድ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው። በመሰረታዊነት ግን የጠቅላይሚኒስቴር ሀሳብ በተግባር ቢመነዘር ጥሩ ነበር። ነገርግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩትን ሲሆኑት በብዛት አይታዮም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለመከላከያ መኮንንኖች ትጥቅ እናስወርዳለን ሲሉም ተናግረዋል። በአን

Source: Link to the Post

Leave a Reply