የአገሪቱ ሠራዊት ወደ መቀለ እየተጠጋ ባለበት በአሁኑ ሠዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በክልሉ ዋና ከተማ ውስጥ ያሉ አመራሮችና ኃይሎች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ የመጨረሻ ያሉትን የሦሰት ቀናት ቀነ ገደብ አስቀመጡ። ጨምረውም በዘመቻው ነዋሪው ከሠራዊቱ ጋር በመተባበር ሊደርስ የሚችል ጉዳትን እንዲከላከል ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ የህወሓት አመራሩና የትግራይ ኃይል እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ የ72 ሰዓታት የመጨረሻ የጊዜ ገደብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቀምጠዋል።
Source: Link to the Post