ጠቅላይ ሚኒስትሩ መተከል ደርሰው ከመጡ በኃላ አገው አማራዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በቡለን ተገደሉ፡፡                 አሻራ ሚዲያ         ታህሳ…

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መተከል ደርሰው ከመጡ በኃላ አገው አማራዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በቡለን ተገደሉ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳ…

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መተከል ደርሰው ከመጡ በኃላ አገው አማራዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በቡለን ተገደሉ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-14/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገዳዮችን ብቻ ሰብስበው ተገዳዮችን ያወገዘ እንደነበር አሻራ ሚዲያ በትዝብት አምዱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የልብ ልብ ያገኘው ይህ ጥፋት ቡድን 96 የሚደርሱ አገው አማራዎችን በግፍ ረሽኗል፡፡ በድባጤም ድባቡ አስፈሪ ሆኗል፡፡ ጉባም የተረጋጋ ነገር የለም፡፡ ግድቡ ሙሉ በሙሉ የቀውስ ማዕከል ሆኗል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ፣የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳድር ቁርጠኛ እና ውጤት ተኮር ስራ ሳይሰራ ቀርቷል፡፡ የአሻራ የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚጠቁሙት ንፅሃንን አይሙቱ ያሉ የአማራ ብልፅግና አመራሮች ውግዘት እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ የቢሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት ከሽፍታው ወገን ሆኖ የንፅሃንን ሞት ይበል ብሎ ፀጥ ብሏል፡፡ የአብይ አስተዳድርም ከቅብ መግለጫ ያለፈ ጠብ የሚል ነገር አልሰራም፡፡ ግድያው በመንግስት መዋቅር እንደሚመራ ራሱ መንግስት አምኗል፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን መፍትሄ አለመምጣቱ ግድያው ይቀጥል የሚል መንግስታዊ ድጋፍ እንዳለው ያሳያል፡፡ እስካሁን ከ60 ሺ በላይ አገው እና አማራ ሲፈናቀል፣ከ600 በላዮች ደግሞ በግፍ ታርደዋል፡፡ ከ2 ሺ በላይ ቤቶችም መቃጠላቸው ይታወቃል፡፡ የህወሓት መውደቅ ሌላኛ ህወኃትን ተክሎ እንዳለፈ የመተከሉ ጉዳይ አረጋጋጭ ነው፡፡ ብልፅግናም ከኢህአዴግ የባሰ አውዳሚ እና ገዳይ ድርጅት መሆኑን መተከል እና ወለጋ ምስክሮች ናቸው ተብሏል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply