ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቅ ሰልፍ በቴልአቪቭ ጎዳናዎች ላይ ተጠናክሩ ቀጥሏል፡፡ የታጋች ቤተሰቦችና የስርዓቱ ተቃዋሚዎች ወደ አደባባዮች በመውጣት በኔታ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቅ ሰልፍ በቴልአቪቭ ጎዳናዎች ላይ ተጠናክሩ ቀጥሏል፡፡

የታጋች ቤተሰቦችና የስርዓቱ ተቃዋሚዎች ወደ አደባባዮች በመውጣት በኔታንያሁ መንግስት ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰንዝረዋል።

መንግስት ታጋች ቤተሰቦቻችንን ያስመልስልን ያሉት ሰልፈኞች ፖሊስ በሰልፈኞቹ ላይ የወሰደውን የሃይል እርምጅም አውግዘዋል።
በሌላ ዜና

እስራኤል በራፋሕ የእግረኛ ወታደራዊ ዘመቻ ከመጀመሯ በፊት ደጋግማ ልታስብበት እንደሚገባ ታላቋ ብሪታንያ አሳሰበች።

የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ዛሬ በሰጡት መግለጫ እስራኤል በራፋሕ ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃ ከመውሰዷ በፊት ጉዳዩን አበክራ ልታጤነው ይገባል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል ።

ከዚህ ቀደምም አሜሪካ፣ ጀርመንና ሳውዲ አረቢያም በተመሳሳይ ድርጊቱን ተቃውመዋል።

አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ ከፍተኛ የሐማስ ባለስልጣንን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ደግሞ እስራኤል በራፋሕ የእግረኛ ውግያውን ካፋፋመች በፓሪስ አስተናጋጅነት ታጋቾችን እና ምርኮኞችን ለመለዋወጥ እየተካሄደ ያለውን ድርድር ሊያጨናግፈው ይችላል ብሏል።

የካቲት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply