ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት “በሌብነት ላይ የጀመረውን ዘመቻ” አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ

በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርብ ጊዜ እየተፈጠሩ ያሉ አጀንዳዎች እና ነውጦች፤ መንግስት “በሌብነት ላይ የጀመረውን” ዘመቻ እንዲያቆም የሚደረጉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናገሩ። መንግስት ሙስናን ለመታገል የጀመረውን ዘመቻ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያስታወቁት በወላይታ ሶዶ ከተማ የተገነባ የዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካ ምርቃት ላይ ትላንት አርብ ታህሳስ 14፤ 2015 ባደረጉት ንግግር ነው። መንግስታቸው ሌብነትን ለመታገል በመነሳቱ፤ “ዋልታ የረገጡ ቡድኖችን” በመጠቀም “ኢትዮጵያን የማመስ” ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል። 

ከውስጥም ሆነ ከውጭ ያሉ አካላት ለእነዚህ ኃይሎች “የፋይናንስ ድጋፍ” በመስጠት፤ “የሚያስተባብራቸውን ጉልበት” እንዲያገኙ እንዳደረጓቸው አብይ ገልጸዋል። “ሌብነት ሩቅ አይደለም፤ ጉያችን ስር ነው ያለው። ጉያችን ስር ያለው ሌብነት እነማንን ቢያስተባብር፤ ትኩረታችንን፣ ስራችንን ለማጨናገፍ እንደሚችል ያውቃል። አሁን የምታዩት ነውጥ ሁሉ ‘የሌብነት ዘመቻው ይቁም’ የሚል ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)  

The post ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት “በሌብነት ላይ የጀመረውን ዘመቻ” አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቁ appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply