ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከገበታ ለሀገር አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከገበታ ለሀገር አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከገበታ ለሀገር አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።

የመንግሥት ሠራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለዚሁ ተግባር እየለገሱ መሆኑ በውይይቱ ወቅት መነሳቱን ከጠቅይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በውጪ ምንዛሬ የባንክ ሂሳቦች ድጋፋቸውን እንደሚያስገቡ ተገልጿል።

በንግዱ ማህበረሰብ አስቀድሞ ቃል የተገባውን ጨምሮ፤ ቀጣይ የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ቀጥለው የታሰበውን የ3 ቢሊየን ብር ድጋፍ ያስገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል።

The post ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከገበታ ለሀገር አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply