ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መተከል ዞን ገብተዋል::የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመተከል ዞን ፓዊ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡በአሁኑ ሰዓትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

https://cdn4.telesco.pe/file/QykD48aif9i7o2RZD40v3AFYpR8_144XS2i0OovFmYdqGjF-37l7U542Hjsxhb2jQqyLZLOUVKaxv16JaniLsu0bG1ovXAFcNmuAYxDLXXHcnmLdOPmr2rq9bbuYlYvaeO6zJs5nNLnulAym9DcB8jQQISlCWPKxxEbIH03ABBKYhowiZBvwUJotY-hEOnRQkMX356H2nHRfn2haNEWTs8vDMAEHG3DjfnbxGwKKg0vyg4bG3hFuj_TQdEBFAQJ9EybtS8QrsknGgtg3FMnHl4lHKsP6uR9kWSUZ03BPu0Cqff3u71evWUF3oy4rFmHKPzIYUrMLIPyS17n1Xm60Fw.jpg

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መተከል ዞን ገብተዋል::

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመተከል ዞን ፓዊ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአካባቢው የህዝብ ተወካዮች እና ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ መሆኑን ጠቁመዋል የአል ዐይን አማርኛ የዜና ምንጮች፡፡

ውይይቱ በዞኑ ተደጋግመው በደረሱ ብሄር ተኮር በዋናነትም የአማራ እና አገው ተወላጆች ጥቃትን የተመለከተ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ የዘገበው ኤፍ.ቢ.ሲ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተዋል ብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply