ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የሃላፊነትጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትርዐቢይ አሕመድ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የተባበ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የሃላፊነት
ጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር
ዐቢይ አሕመድ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የተባበሩት ዓረብ
ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ አለዎት
መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የሀላፊነት ጊዜያቸው
ስኬታማ እና አገሪቱን ወደ ተሻለ እድገት እና ብልጽግና
የሚያሻግሩበት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች
ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን የሀገሪቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ
ቤት በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 06 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply