ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቱርክ ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ዛሬ ባሰፈሩት መልዕክት “ከቱርክና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ እኔና የልዑካን ቡድኔ ከፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ዛሬ አካሂደናል።

የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ሁሌም በመከባበር ላይ የተመሠረተ ነው። ትብብራችን በገንቢ ተሳትፎ ላይ በመመሥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሁለት ዓመታት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬና ነገ በዋና መዲናይቱ ኢስታሙብል እንደሚካሄድ ተመልክቷል፡፡

በአፍሪካ ውስጥ ትልቅ የንግድ ግብይት እንዲኖራት በመስራት ላይ የምትገኘው ቱርክ፣ አፍሪካ ውስጥ ከ30 በላይ ኤምባሲዎችን መክፈቷ ተነገሯል፡፡

የቱርክ ፕሬዚዳንት ታይፕ ኤርዶጋንም ከእኤአ 2003 ጀምሮ 28 ጊዜያት አፍሪካን የጎበኙ መሪ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply