You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሊሰጡ ነው =======#======= መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሊሰጡ ነው =======#======= መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሊሰጡ ነው =======#======= መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ መጋቢት 19/2015 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም መደበኛ ስብሰባ ላይ፤ የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ማስገባታቸውን ምንጮች ነግረውኛል ሲል “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት፤ የዓመቱን የመጀመሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ባሳለፍነው ሕዳር ወር መጀመሪያ ላይ ሲሆን፤ በነገው ዕለት ለሚካሄደው ተመሳሳይ ስብሰባም የፓርላማ አባላት ጥያቄዎቻቸውን “በአስቸኳይ” እንዲያቀርቡ የተደረገው ከሳምንት በፊት እንደሆነ ተነግሯል። ከአንድ ወር ዕረፍት በኋላ የተመለሱት እነኚሁ የፓርላማ አባላት፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 9/2015 በተወካዮች ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በነበራቸው ስልጠና ይኸው እንደተነገራቸው ምንጮቹ ገልጸዋል። ይህንኑ ያረጋገጡት አንድ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፓርላማ አባል፤ “ ‘በአስቸኳይ አስገቡ’ ብለው ባለፈው ቅዳሜ ነገሩን። ቀን ላይ ነግረውን፤ ‘እስከ ማታ ድረስ’ አሉን” ሲሉ ለጥያቄ ማቅረቢያ የተሰጠው አጭር ጊዜ እንደነበር አስታውሰዋል። የፓርላማ አባሉ አክለውም፤ “ብዙዎቻችን ‘አይሆንም፤ ተረጋግተን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርብ አይነት ጥያቄ በአግባቡ ማዘጋጀት አለብን’ ስንል እስከ እሁድ አመሻሽ ድረስ አቅርቡ ተባለ” ሲሉ ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜው በአንድ ቀን እንዲራዘም መደረጉን አስረድተዋል። በዚህ አካሄድ እስከ ባለፈው ሳምንት እሁድ አመሻሽ ድረስ፤ የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች አስገብተው ማጠናቀቃቸውንም ጨምረው ገልጸዋል። የጥያቄ ማቅረቢያ ጊዜው ካበቃ በኋላ ያዘጋጁትን ጥያቄ ለማቅረብ የሄዱ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ጥያቄ ማስገባት አለመቻላቸውም ተነግሯል። ከእነዚህ የፓርላማ አባላት መካከል አንዱ፤ “አርፍጄ ሰኞ ጠዋት ላስገባ ስሄድ፤ already ጥያቄዎች ተመርጠው አልቀዋል። ለእርሳቸው ተልኳል አሉኝ” ሲሉ የዛሬ ሳምንት ሰኞ ረፋድ ጥያቄ ለማስገባት ሞክረው ያገኙትን ምላሽ አስረድተዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ፤ “ማንኛውም የቃል መልስ የሚፈልግ ጥያቄ የሚያቀርብ አባል፤ ጥያቄውን ቢያንስ ከአስር ቀን በፊት ለአፈ ጉባኤው በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት” ሲል ይደነግጋል። አፈ ጉባኤው በምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች መርምረው ሊቀበሉት ወይም ውድቅ ሊያደርጉት እንደሚችሉም ያስረዳል። ጥያቄዎቹ ለአፈ ጉባኤው ከቀረቡ በኋላ፤ አፈ ጉባኤው በፓርላማው የመንግስት ዋና ተጠሪ ከሆኑት ግለሰብ ጋር በመሆን ጥያቄዎችን የመለየት ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ አንድ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራር ተናግረዋል። ጥያቄዎች በዚህ መልኩ ከተለዩ በኋላ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚቀርቡም እኚሁ አመራር አክለዋል። በነገው ዕለት በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል፤ “የኑሮ ውድነትን የተመለከቱ ይኖራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ጠቁመዋል። “ወደ አዲስ አበባ አትገቡም እየተባለ ወደ አማራ ክልል የሚመለሱ ሰዎች” ጉዳይን የተመለከቱ ጥያቄዎችም፤ በነገው የፓርላማ ስብሰባ ጥያቄ ሊቀርብ እንደሚችል ምንጮች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ለነገው መደበኛ ስብሰባ እስከ ትላንት አመሻሽ ድረስ ጥሪ እንዳልደረሳቸው፤ አራት የፓርላማ አባላት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ለአፈ ጉባኤው ያቀረቡት ጥያቄ የተመረጠላቸው የፓርላማ አባላት፤ ስብሰባው ከመካሄዱ 48 ሰዓታት በፊት በስልክ ተደውሎ ይነገራቸው እንደነበርም አስታውሰዋል። ዘገባው የአዲስ ማለዳ ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply