ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በ39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ናይሮቢ ገቡ

ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በ39ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግሥታት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኬንያ መዲና ናይሮቢ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጉባኤው መሪዎቹ በአካባቢው የሚከሰተውን ድርቅ ማሸነፍ በሚቻልበት ኹኔታ፣ በሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply