ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ሰይመዋል።
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል።
በዚሁ መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሰየሙ የዕጩ ሰብሳቢ መልማይ ኮሚቴ አባላት፡-

- ቀሲስ ታጋይ ታደለ……………….. ሰብሳቢ
- ተከተል ዮሐንስ (ፕ/ር) ………….አባል
- ባዩህ በዛብህ…………. አባል
- ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) …………. አባል
- ካሳሁን ፎሎ…………. አባል
- ርግበ ገብረሃዋርያ…………. አባል
- እንግዳዬ እሸቴ…………. አባል
- መላኩ እዘዘው (ኢ/ር) …………. አባል ናቸው።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴው ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፤ በቅርቡም ጥቆማ መቀበል ይጀምራል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ የነበሩት ብርቱካን ሚዴቅሳ፤ በጤና ችግር ምክንያት ከነሐሴ 1/2015 ጀምሮ ከቦርዱ ሰብሰቢነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post