ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ ሀገራት ለተወለዱ ወይም  ሁለተኛው ትውልድ የዳያስፖራ አባላት ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ  ጥሪ  አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን ጥሪ ያስተላለ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ ሀገራት ለተወለዱ ወይም  ሁለተኛው ትውልድ የዳያስፖራ አባላት ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ  ጥሪ  አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን ጥሪ ያስተላለፉት ዛሬ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በጨበራ ጩርጩራ መካነ አራዊት ውስጥ የተገነባውን የጎብኚዎች ማረፊያና መዝናኛን ወይም የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።

በዚህም ጥሪ መሠረት በውጭ ሀገራት የተወለዱ ሁለተኛው ትውልድ የዳያስፖራ አባላት በሦስት ዙር ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ጠይቀዋል።እነዚህም የዳያስፖራ አባላት ችግኝ መትከልን ጨምሮ በሌሎች ሥራዎች እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅን ዛሬ መርቀው ሲከፍቱም የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅ በውበቱ በሀገሪቱ የመጀመሪያው እንደሆነ ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 13  ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply