ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራት በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርህ እንዲገዙ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራት በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርህ እንዲገዙ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራት በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርህ እንዲገዙ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ አገራት በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት መርህ መገዛት እንዳለባቸው ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ከመንግሥታቱ ማኅበር መሥራች አባልነት ጀምሮ ለዘርፈ ብዙ ዓለም አቀፍ ትብብር እና ለዓለም መረጋጋት ቃል የገባቻቸው መርሆዎች እና የፈረመቻቸው ሕግጋት ጽኑ እና የማይገሰሱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በመሆኑም አገሪቱ በዓለም አቀፍ ሥርዓት መሠረት የሕጎች ጠባቂ ለመሆኗ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ተእልኮዎች ውስጥ የምታደርጋቸው ተሳትፎዎች ምስክር ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለመርዳት ያለውን ፍላጎት እንደምታደንቅ ጠቁመው፣ ይህ ግን ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት አድርጎ ሊተገበር እንደሚገባው በአጽንኦት ገልጸዋል። በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያ መንግሥት የድጋፍ ጥሪ እስኪያቀርብ ድረስ ሊጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ከሁለት ዓመታት በፊት አጠቃላይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ይፋ ሲያደርግ ሰላም እና ብልጽግናን ለማምጣት በማሰብ መሆኑን አስታውሰው፣ ከውጭ አገራት ጋር ሰላም ለመፍጠር የተደረጉ ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሁሉን ነገር በራሱ ፍላጎት ብቻ የማድረግ አባዜ የተጠናወተው ሕወሓት ግን የለውጡን ሂደት በሙሉ በማጣጣል፣ በማደናቀፍ እና ኃይልን በመጠቀም ወደ ሥልጣን ለመመለስ መሞከሩን አመልክተዋል። በተመሳሳይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይፋ ያደረገው ሪፖርት ከዚህ ቀደም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት የሚያረጋግጥ መሆኑንም የኢቢሲ ዘገባ አመልክቷል። ተግባሩ ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያ እየፈፀመ ያለው ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል ምን ያህል አንደሆነም የዓለም ሕዝብ በድጋሚ ያረጋገጠበት ነው በማለት ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉም አስታውቋል። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እንደአብነት በኦሮሚያ ጉሊሶ፣በደቡብ ጉራ ፈርዳ፣ በመተከል በርካታ ወረዳዎች በአማራ ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ፍጅት መካሄዱ ይታወቃል። በመተከል አሁንም ድረስ የዘር ማጥፋት ወንጀሉ በኦነግ ሸኔ፣በጉምዝ ታጣቂዎች፣በመንግስት አካላት ታግዞ እየቀጠለ መሆኑ እየተገለፀ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply