ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰጡት ሹ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰጡት ሹመት መሰረትም:_ አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም፣ ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር፣ ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ገዱ አንደዳርጋቸውን ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚንስትር አድርገው ሾመዋል። በተመሳሳይ ዜና አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሾመዋል። ርእሰ መሥተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለሌላ ኃላፊነት መታጨታቸውን ተከትሎ ለክልሉ ምክር ቤት የስልጣን መልቀቂያ በማስገባታቸው ጥያቄያቸው በምክር ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን አብመድ ዘግቧል። ይህንን ተከትሎ ነው በምትካቸው የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በእጩነት ያቀረባቸው በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አገኘው ተሻገር የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply