ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አዲስ ለተመረጡት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቀጣዩ ጊዜ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የሚጎለብትበት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸው፤ ለተመራጩ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ስኬታማ የሥራ ዘመን ተመኝተዋል። ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply