ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱ ተገቢ ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱ ተገቢ ነው ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር ፡- 16/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱ ተገቢ ነው” ሲሉ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ተናገሩ። በኢትዮጵያ መንግስት እየተወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ እንዴት እንደሚመለከቱት የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚፈልጉትን አካላት መቅጣት አለባቸው ብለዋል፡፡ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር እርምጃ ትክክለኛ መሆኑን ጠቁመዋል። የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ከሀዲው የህወሓት ቡድን የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስና የስልጣን ፍላጎቱን ለማርካት እንደሚፈልግ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የፌዴራል መንግስትን በማዳከም እግሩ ስር ለማንበርከክና ማዕከላዊ መንግስትን መቆጣጠር ይፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከዚህ አንጻር የነበራቸው ሁለት ምርጫ ብቻ ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የመጀመሪያው ከዚህ ቡድን ጋር በተናጠል መደራደር ሲሆን ይህ ምርጫ አገሪቷን የሚበትን ምርጫ ነው ብለውታል። ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ህግ ማስከበርና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረጡት ሁለተኛውን ምርጫ ነው ሲሉ የተወሰደውን እርምጃ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply