ጠቅላይ ፍ/ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብት ይግባኝ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምላሽ እንዲሰጥ ቀጠሮ ሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ…

ጠቅላይ ፍ/ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብት ይግባኝ ላይ ዐቃቤ ሕግ ምላሽ እንዲሰጥ ቀጠሮ ሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት ፤ ዐቃቤ ሕግ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ መስርቶት የነበረውን ሦስት ክሶችን ማስረጃ መርምሮ ፍርድ ቤቱ በ1ኛ እና በ2ኛ ክስ ጋዜጠኛ ተመስገንን ሙሉ በሙሉ በነጻ ያሰናበተው ሲሆን ፤ በሦስተኛው ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44 (1) 2) እና 257 (ሠ) ስር የተመለከተውን ፤ በአዎጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 ስር ክሱን እንዲከላከል ብይን መስጠቱ የሚታወቅ ነው። በዚህም መሠረት ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን እንዲከላከል ብይን የተሰጠበት ድንጋጌ የዋስትና መብት የማይከለክል እና ጥፋተኛ ነው እንኳን ቢባል የሚጣልበት ቅጣት ፤ የግዴታ ስራ ወይም የገንዘብ መቀጮ የሚጥል በመሆኑ እንዲሁም ቀደም ሲል ዐቃቤ ህግ ዋስትና ለማስከልከል በዋናነት ያቀረባቸው ምክንያቶች የክሶቹን ተደራራቢነት እና የቅጣቱን ክብደት መነሻ አድርጎ ከመሆኑ አንጻር አሁን ተከላከል የተባለበት የህግ ድንጋጌ የተጠቀሱት ምክንያቶች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚያደርግ በመሆኑ ፤ በተጨማሪም ቀደም ሲል የዋስትናው ጉዳይ ሲታይ ከነበረበት ነባራዊ ሁኔታ የተለወጠ (አዲስ ነገር) ያለ በመሆኑ ፤ የደንበኛችን የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብት ሊከበር ይገባል በማለት ፤ ጠበቃ ቤተማሪያም አለማየሁ እና ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ፤ ለልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት አመልክተዋል። ሆኖም ግን ፤ ፍርድ ቤቱ በጠቅላይ ፍ/ቤት የዋስትናው መብት ከዚህ ቀደም ቀሪ የሆነ በመሆኑ ፤ በዚህ ችሎት በድጋሚ ሊቀርብ ስለማይችል ጥያቄውን አልቀበልም በማት ውድቅ አድርጎታል። ይሁን እንጂ ፤ ይህ ውሳኔ አግባብ አይደለም ፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትእዛዝ የሕግና የፍሬ ነገር ስህተት ያለበት በመሆኑ ፤ የደንበኛችን ጉዳይ በአግባቡ ይታልን በማለት ጠበቃ ቤተማሪያም አለማየሁ እና ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሜ ችሎት ፤ ለፍርድ ቤቱ በቃል እና በጽሁፍ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። የዋስትና መብት መሰረታዊ መብት በመሆኑና በተለይም ለተከሳሽ በሚጠቅም እንዲሁም በጠባቡ ሊተረጎም የሚገባ የመብት አይነት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የይግባኛ አቤቱታችን በአፋጠኝ በመመልከት የስር ፍ/ቤትን ትእዛዝ በመሻር የይግባኝ ባይን የዋስትና መብት እንዲፈቅድ ወይም የስር ፍ/ቤት የዋስትናውን ጉዳይ በድጋሚ ተመልክቶ የመሰለውን እንዲወስን ትእዛዝ ወደ ስር ፍ/ቤት እንዲመልስልን እንጠይቃለን በማለት ጠበቆች አመላክተዋል ። ጉዳዩን የተመለከተው እና ይግባኙን የሰማው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፤በተከሳሽ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቆች በኩል የቀረበው ይግባኝ አግባብ ነው ፣ ያስቀርባል በማለት በመወሰን ፤ ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብት ይግባኝ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ለጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። አሻራ ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply