You are currently viewing ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ስለ ታጋይ ጥላሁን አበጀ የእስር ሁኔታ የሚከተለውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል! ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ህዝባዊ ኃይ…

ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ስለ ታጋይ ጥላሁን አበጀ የእስር ሁኔታ የሚከተለውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል! ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ህዝባዊ ኃይ…

ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ስለ ታጋይ ጥላሁን አበጀ የእስር ሁኔታ የሚከተለውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል! ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ህዝባዊ ኃይል አመራርና አባላት ላይ ከዋናው ጠላት እስከ ተከፋይ አክቲቪስቶች ድረስ ዘመቻ የተከፈተባቸው ገና ምስረታው ለህዝብ ይፋ ሳይደረግ ነው። ቀጥሎም ህግ ማስከበር በሚል የዳቦ ስም ጦር ተላከባቸው። የህዝባዊ ኃይሉ አመራርና አባላት ምንም የህግ ጥሰት እንዳልፈፀሙ እያወቁ የመንግስት እብደት እስኪረግብ ከእይታ መሰወርን መርጠው ከአደባባይ ገለል ብለው የቆዩ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መደበኛ ስራቸውን ለማከናወን ወደ አደባባይ ሲወጡ እብደቱ ያለቀቀው መንግስት ማፈን ስራው አድርጎታል። ዛሬም (ጥቅምት 2/2015) ጥላሁን አበጀን ባህር ዳር ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ወስደውታል። በአሁኑ ሰዓት የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አይታወቅም ብሏል። ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ስለ አማራ ብሎም ስለ ሀገር እና ስለ ወገን ሲል የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አደረጃጀትን በማዋቀር እና በማሰልጠን በተለይም በአማራ የህልውና ትግል ላይ የድርሻውን በማበርከት እየታገለ መሆኑ ቢታዋቅም በብአዴናዊያን የለዬለት ክህደት ከመስከረም 11/2015 ጀምሮ በባህር ዳር በግፍ ታስሮ እንደሚገኝ እንዲሁም ጥቅምት 1/2015 በነበረው ችሎትም የዐቃቢ ህግ አቤቱታ ለጠበቆች ሳይደርስ እና አስተያዬትም ሳይሰጥበት የባህር ዳር ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ ለመመስረት በዐቃቢ ህግ እንደተጠየቀ በመግለጽ 15 ቀናትን መፍቀዱ ይታወሳል። የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ውስጥ ገብቷል በሚል በተለያዩ አካባቢዎች በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ በመሳተፍ እና በመሰልጠን ብሎም ግንባር ድረስ በማቅናት ተጋድሎ በማድረግ በሚታወቁ ፋኖዎች ላይ በህግ ማስከበር ስም ጦርነት በመክፈት ጭምር ግድያ መፈጸሙ፣ በሽህ የሚቆጠሩም በተለያዩ አካባቢዎች በግፍ እስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply