ጠንካራ የሆነ የዲሞክራሲ ተቋም ካልተፈጠረ ሰብአዊ መብት ማክበር አይቻልም ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ ጠንካራ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት ካልተፈጠሩ የመብት ጥሰቶችን ማስቆም ከባድ መሆኑን ነው የተገለጸው፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ በኢትዮጵያ ገለልተኛ እና ጠንካራ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት ካልተፈጠሩ ሰብአዊ መብቶች ማክበር አይቻልም ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በሃገሪቱ በርካታ ግጭቶች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መኖራቸው የጠቀሱት ኮሚሽነሯ እነዚህን ግጭቶች መፍታት እና ማስቆም የሚችሉ ጠንከራ ተቋማት ሊኖሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከዚህ አንጻር ደርሼበታለሁ ወደ ሚለው ደረጃ አለመድረሱን የተናገሩት ራኬብ መሰለ ተቋሙን ገለልተኛ እና ዘላቂ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በባላፉት ሶስት እና አራት አመታት የአገሪቱን በሰብአዊ መብት አጀንዳ በተወሰነ መልኩ ተጽኖ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚያወጣቸው ምክረ ሃሳቦች በአስፈጻሚው አካል በተሻለ ሁኔታ መፈጸም ይገባቸዋል ያሉት ምክትል ኮሚሽኗ፡ ተጎጂዎችን ከመካስ እና ፍትህን ከማስፈን አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቅበናል ብለዋል፡፡

የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ሂደት ነው ያሉት ራኬብ መሰለ አገራዊ ምክክር ሲጀመር ሁነታዎች እየተለወጡ መሄዳቸው አይቀርም ሲሉ ገልጻል፡፡

ከገለልተኝነት አንጻር ኮሚሽኑ ምንም ጥያቄ የሚነሳበት ስራ አለመስራቱን የሚናገሩት ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እስካሁን ኮሚሽኑ ካቀረባቸው ምክረ ሃሳቦች መካከል መአስፈጻሚው አካል ውድቅ የሆነበት አንድ ብቻ መሆኑን ተባግረዋል፡፡

በአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን አደረጃጀት እና ስራ የሚገመግመው መቀመጫውን ጄኔቫ ሲውዘርላን ያደረገው Global Alliance of national human right institutions የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን የኤ ደረጃ እንደሰጠው ነው የተገለጸው፡፡

ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 26  ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply