ጠገዴ አርማጭሆ በጎ አድራጎት ማህበር ከአባላቱ ገንዘብ በመሰብሰብ የዘማች ቤተሰቦችን አረም እያሳረመ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

ጠገዴ አርማጭሆ በጎ አድራጎት ማህበር ከአባላቱ ገንዘብ በመሰብሰብ የዘማች ቤተሰቦችን አረም እያሳረመ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሀሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ አንዳርጋቸው ደሴ እንዳሉት የዘማች ቤተሰቦችን በሁሉም ቀበሌዎች የሚገኝ ማሳ እየታረመላቸው መሆኑን ገልፀዋል። በዛሬው እለት በጠገዴ አርማጭሆ በጎ አድራጎት ማህበር በተገኘ ገንዘብ ከ20 በላይ የጉልበት ሰራተኞችን በመቅጠር የዘማች ምንይሉ አዱኛ የሰሊጥ ማሳ የታረመ ሲሆን ይህም በደስታና በወኔ ተልዕኮውን እንዲወጣ ያደርገዋል ብለዋል። የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ወንደወሰን ንጉሴ በበኩላቸው በሃገራችን ላይ የተጋረጠብን ችግር ሁሉም የኔ ነው በማለት አካባቢውን በንቃት መጠበቅ ፣ የዘማች ቤተሰቦችን አረም በማረምና ቤተሰቦቻቸውን በመንከባከብ ፣ድጋፍ ማሰባሰብና ጁንታን ለመደምሰስ ግንባር እስከመሰለፍ ድረስ ዝግጁ መሆን አለብን ብለዋል። የዘማች ምንይሉ ወንድም ወጣት ጌታቸው አዱኛ እንደተናገረው ልማታችን እንዳይቋረጥ ወረዳችንና ህብረተሰቡ ከተለያዩ በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመቀናጀት ድጋፋቸው እንዲህ ሚቀጥል ከሆነ ከወንድሜ ጎን በመሰለፍ ጠላትን እስከመጨረሻው እፋለማለሁ ብሏል። በተመሳሳይ በታች አርማጭሆ ወረዳ በህዳሴ 02 ቀበሌና በከንባው ቀበሌም በአመራር አብዱል ቃድር ሃሰንና በቀበሌው አስተዳዳሪ አስተባባሪነት ህብረተሰቡ በላቀ ተሳትፎ በዘማች አዳነ እጅጉ የሰሊጥ ማሳ በመገኘት የአረም ስራ እንዳከናወኑና በሌሎች የዘማች ስራዎችም ህብረተሰቡ የተባበረ ክንዱን በማሳየት ጀግንነትን ከድል ጋር በማቀናጀት ተሳትፎው እንደቀጠለ ስለመሆኑ ተገልጧል። ከዚህም በተጨማሪ የታች አርማጭሆ ወርዳ የምክር ቤት ጽ/ቤትና የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ለዘማች ቤተሰቦች አረም የማስወገድ ስራ ማከናወናቸውን የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ታሪክ ከፍያለው ተናግረዋል። ዘገባው የታች አርማጭሆ ወረዳ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply