ጠ/ሚ አብይ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስለሚገኘው ኦፐሬሽን፣ ስለ ሰብዓዊ ድጋፎች፣ የክልሉን ነዋሪዎች ደህንነት ስለማስጠበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም…

ጠ/ሚ አብይ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስለሚገኘው ኦፐሬሽን፣ ስለ ሰብዓዊ ድጋፎች፣ የክልሉን ነዋሪዎች ደህንነት ስለማስጠበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም…

ጠ/ሚ አብይ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስለሚገኘው ኦፐሬሽን፣ ስለ ሰብዓዊ ድጋፎች፣ የክልሉን ነዋሪዎች ደህንነት ስለማስጠበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/3/13/ዓ.ም ባህር ዳር ሕግ ማስከበር ተልዕኮውን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል ልዩ ሀይልና የሚኒሻ አባላት ባለፉት ጥቂት ቀናት ያስመዘገበው ድል የሚደነቅ መሆኑን ጠ/ሚ አብይ አህመድ ተናገሩ ። … ሠራዊታችን ትናንት ምሽት በአዲግራት ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ዛሬ ደግሞ አዲግራትን ከሕወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ ነፃ አውጥቷል ብለዋል። የፌደራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው ከተማዎችና አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች፣ በጸጥታ ኃይሎች ጥበቃ እየተደረገላቸው ወደ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው መመለስ መጀመራቸውንም ተናግረዋል። ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን፣ ሰብአዊና ማኅበራዊ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን መንገድ እናመቻቻለን ሲሉም ገልጸዋል። የሰብአዊ ድጋፍ ክንውኖችን ለመከታተል በፌደራል መንግሥት የተዋቀረው ከፍተኛ ኮሚቴ፣ ተመጣጣኝ እና ወቅታዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስችል መረጃን እንዲያሰባስቡ ተጨባጭ ሁኔታውን የሚያጣሩ ልዑካንን ወደ ስፍራው ልኳል። በተጨማሪም፣ ይህ ኮሚቴ ባለፉት ቀናት መኖሪያቸውን ጥለው የተሰደዱትን ዜጎች ሁሉ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና ለማቋቋም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መሥራቱን ይቀጥላል። የፌደራል መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ አጠቃላይ ደኅንነት እና ጤንነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ስለ ሆነ፣ በትግራይ ክልል መረጋጋት እንዲሰፍን እና ዜጎቻችን ከጉዳት እና እጦት ነፃ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply