ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ ቦታ የላትም አሉ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ ቦታ የላትም አሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ ቦታ የላትም አሉ፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የትዊተር መልዕክታቸው የትግራይ ሕዝብ ሆነ ማንኛውም ዜጋ የወንጀለኞች መሸሸጊያ አይሆንም ብለዋል፡፡
 
አንቀጽ 51 በመጥቀስም የፌደራል መንግስቱ ህገመንግስቱን ያስከብራል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፡፡
 
እንዲሁም መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት በፈጸመው ቡድን ላይ የህግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃዎችንም ይወስዳል ብለዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨረሻም ወንጀል የፈጸሙ አካላትን ከተሸሸጉበት በማውጣት መላው የሃገሪቱ ህዝብ ወደ ብልጽግና ጎዳና እንመራለን ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

The post ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ለወንጀለኛ ቦታ የላትም አሉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply