
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክን መረቁ፡፡
በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የፓርኩ የመጀመሪያ ምዕራፍ 75 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ 125 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው ተብሏል፡፡
ፓርኩ በቅርቡም ከአራት ሺህ በላይ ሠራተኞችን ለመቀበል ልየታ መሥራቱን የታወቀ ሲሆን በሙሉ አቅሙ በሁለት ፈረቃ ሲሠራ እስከ 10 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ከአብመድ ያገኘነው ተጨማሪ መረጃ ያመለክታል።
የሥራ ዕድል ፈጠራው ሁለተኛ ምዕራፍ ሼድ ሲጠናቀቅም የመጀመሪያው ከሚፈጥረው የሥራ ዕድል በእጥፍ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
ፓርኩ በአካባቢው ለነበሩ የልማት ተነሺዎች ቅድሚያ የሥራ ዕድል እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
በአላዛር ታደለ
The post ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክን መረቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post